Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ቆሮንቶስ 3:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ኀይ​ላ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ሆነ ከእኛ ከራ​ሳ​ችን እንደ ሆነ አድ​ር​ገን ምንም ልና​ስብ አይ​ገ​ባ​ንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፣ በራሳችን ብቃት ከእኛ ነው የምንለው አንዳች ነገር የለንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን የሚሆን አንዳችን ነገር ልናስብ እኛ የበቃን አይደለንም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 አገልግሎታችንን መፈጸም እንድንችል ብቁ የሚያደርገን እግዚአብሔር ነው እንጂ እኛስ በገዛ ራሳችን ምንም ለማድረግ ብቁ አይደለንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ቆሮንቶስ 3:5
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮሴ​ፍም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከገ​ለ​ጸ​ለት ሰው በቀር መተ​ር​ጐም የሚ​ችል የለም” ብሎ ለፈ​ር​ዖን መለ​ሰ​ለት።


ደግ​ሞም አንድ ልብ ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል የሆ​ነ​ውን የን​ጉ​ሡ​ንና የአ​ለ​ቆ​ቹን ትእ​ዛዝ ያደ​ርጉ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ነ​ርሱ ላይ ሆነ።


በእ​ና​ንተ ላይ የሚ​ነሡ ሊመ​ል​ሱ​ላ​ች​ሁና ሊከ​ራ​ከ​ሯ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ችሉ እኔ አፍ​ንና ጥበ​ብን እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።


እነሆ፥ እኔ የአ​ባ​ቴን ተስፋ ለእ​ና​ንተ እል​ካ​ለሁ፤ እና​ንተ ግን ከአ​ር​ያም ኀይ​ልን እስ​ክ​ት​ለ​ብሱ ድረስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከተማ ተቀ​መጡ።”


እኔ የወ​ይን ግንድ ነኝ፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹም እና​ንተ ናችሁ፤ በእኔ የሚ​ኖር እኔም በእ​ርሱ፥ ብዙ ፍሬ የሚ​ያ​ፈራ እርሱ ነው፤ ያለ እኔ ምንም ማድ​ረግ አት​ች​ሉ​ምና።


አሕ​ዛ​ብም እን​ዲ​ያ​ምኑ ክር​ስ​ቶስ በቃ​ልም በሥ​ራም ያደ​ረ​ገ​ል​ኝን እና​ገር ዘንድ እደ​ፍ​ራ​ለሁ።


ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አሁን እኔ ባለ​ሁ​በት አለሁ፤ ለእ​ኔም የሰ​ጠኝ ጸጋው ለከ​ንቱ የሆ​ነ​ብኝ አይ​ደ​ለም፤ እኔም ከሁሉ ይልቅ ደከ​ምሁ፤ ነገር ግን በእኔ ላይ ያደ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አጸ​ናኝ እንጂ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰጠኝ ጸጋ መጠን እንደ ብልህ የጠ​ራ​ቢ​ዎች አለቃ ሆኜ እኔ መሠ​ረት ጣልሁ፤ ሌላ​ውም በእ​ርሱ ላይ ያን​ጻል፤ እያ​ን​ዳ​ንዱ ግን በእ​ርሱ ላይ እን​ዴት እን​ደ​ሚ​ያ​ንጽ ይጠ​ን​ቀቅ።


እኔ ተከ​ልሁ፤ አጵ​ሎ​ስም አጠጣ፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳ​ደገ።


እር​ሱም፥ “ጸጋዬ ይበ​ቃ​ሀል፤ ኀይ​ልስ በደዌ ያል​ቃል” አለኝ፤ የክ​ር​ስ​ቶ​ስም ኀይል በእኔ ላይ ያድር ዘንድ በመ​ከ​ራዬ ልመካ ወደ​ድሁ።


የሞት መዓዛ የሚ​ገ​ባ​ቸው ለሞት፥ የሕ​ይ​ወት መዓዛ የሚ​ገ​ባ​ቸ​ውም ለሕ​ይ​ወት ናቸው፤ ነገር ግን ይህ የሚ​ገ​ባው ማነው?


ነገር ግን ከእኛ ያይ​ደለ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ገኘ ታላቅ ኀይል ይሆን ዘንድ በሸ​ክላ ዕቃ ውስጥ ይህ መዝ​ገብ አለን።


ለሚ​ወ​ደው ሥራ የሚ​ረ​ዳ​ችሁ እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታ​ውን ይፈ​ጽ​ም​ላ​ችሁ።


በሚ​ያ​ስ​ች​ለኝ በክ​ር​ስ​ቶስ ሁሉን እች​ላ​ለሁ።


ብዙ ሰዎች የመሰከሩለትን ከእኔም የሰማኸውን ሌሎችን ደግሞ ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ።


በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፤ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች