Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 30:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ዳዊ​ትም የበ​ጉ​ንና የላ​ሙን መንጋ ሁሉ ወሰደ፤ ምር​ኮ​ው​ንም በፊቱ ነዱ፤ ያንም ምርኮ “የዳ​ዊት ምርኮ” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እንዲሁም ዳዊት የበጉን፣ የፍየሉንና የላሙን መንጋ ሁሉ ወሰደ፤ ሰዎቹም “ይህ የዳዊት ምርኮ ነው” እያሉ መንጋውን ከሌሎች ከብቶች ፊት ለፊት ይነዱ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እንዲሁም ዳዊት የበጉን፥ የፍየሉንና የላሙን መንጋ ሁሉ ወሰደ፤ ሰዎቹም “ይህ የዳዊት ምርኮ ነው” እያሉ መንጋውን ከሌሎች ከብቶች ፊት ለፊት ይነዱ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 የከብት፥ የበግና የፍየል መንጋዎችንም ሁሉ አገኘ፤ ተከታዮቹም እንስሶቹን በፊታቸው እየነዱ “ይህ ሁሉ የዳዊት ምርኮ ነው!” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ዳዊትም የበጉንና የላሙን መንጋ ሁሉ ወሰደ፥ ከራሱም ከብት ፊት እየነዳ፦ ይህ የዳዊት ምርኮ ነው አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 30:20
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የከ​ብ​ቶ​ቹ​ንም በረት አፈ​ረሱ፤ እጅግ ብዙ በጎ​ች​ንና ግመ​ሎ​ች​ንም ወሰዱ፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተመ​ለሱ።


ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥና ሕዝ​ቡም ምርኮ ይወ​ስዱ ዘንድ መጡ፤ ብዙ ከብ​ትና ልዩ ልዩ ዕቃም፥ ልብ​ስም፥ እጅ​ግም ያማረ ዕቃ አገኙ፤ ማረ​ኩ​ትም፤ ምር​ኮ​ውም ብዙ ነበ​ርና ምር​ኮ​ውን እየ​ሰ​በ​ሰቡ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ቈዩ።


ስለ​ዚ​ህም እርሱ ብዙ​ዎ​ችን ይወ​ር​ሳል፤ ከኀ​ያ​ላ​ንም ጋር ምር​ኮን ይከ​ፋ​ፈ​ላል፤ ነፍ​ሱን ለሞት አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ልና፥ ከዐ​መ​ፀ​ኞ​ችም ጋር ተቈ​ጥ​ሮ​አ​ልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎ​ችን ኀጢ​አት ተሸ​ከመ፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ተሰጠ።


ነገር ግን በወ​ደ​ደን በእ​ርሱ ሁሉን ድል እን​ነ​ሣ​ለን።


ዳዊ​ትም ደክ​መው ዳዊ​ትን ይከ​ተ​ሉት ዘንድ ወዳ​ል​ቻሉ፥ በቦ​ሦር ወንዝ ወዳ​ስ​ቀ​ራ​ቸው ወደ ሁለቱ መቶ ሰዎች መጣ፤ እነ​ር​ሱም ዳዊ​ትን ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ሊቀ​በሉ ወጡ፤ ዳዊ​ትም ወደ ሕዝቡ በቀ​ረበ ጊዜ ደኅ​ን​ነ​ቱን ጠየ​ቁት።


ዳዊ​ትም ወደ ሴቄ​ላቅ በመጣ ጊዜ ለይ​ሁዳ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ለወ​ዳ​ጆቹ፥ “እነሆ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶች ምርኮ በረ​ከ​ትን ተቀ​በሉ” ብሎ ከም​ር​ኮው ላከ​ላ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች