Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 28:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ሳሙ​ኤ​ልም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከራ​ቀህ፥ ወደ ባል​ን​ጀ​ራ​ህም ከተ​መ​ለሰ ለምን ትጠ​ይ​ቀ​ኛ​ለህ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤ “ታዲያ እግዚአብሔር ከራቀህ፣ ጠላትም ከሆነህ ለምን ትጠይቀኛለህ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤ “ታዲያ ጌታ ከራቀህ፥ ጠላትም ከሆነህ ለምን እኔን ትጠይቀኛለህ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ሳሙኤልም ሳኦልን እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር ተለይቶህ ጠላትህ ከሆነ በኋላ እኔን ስለምን ታስጠራኛለህ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ሳሙኤልም አለ፦ እግዚአብሔር ከራቀህ ጠላትም ከሆነህ ለምን ትጠይቀኛለህ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 28:16
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካል​ረ​ዳሽ እኔ እን​ዴት እረ​ዳ​ሻ​ለሁ? ከአ​ው​ድ​ማው ወይስ ከመ​ጭ​መ​ቂ​ያው ነውን?” አለ።


ዳሌጥ። ቀስ​ቱን እንደ ተቃ​ዋሚ ጠላት ገተረ፤ እንደ ባላ​ጋ​ራም ቀኝ እጁን አጸና፤ በጽ​ዮን ሴት ልጅ ድን​ኳን ለዐ​ይኑ የሚ​ያ​ም​ረ​ውን ሁሉ ገደለ፤ መዓ​ቱ​ንም እንደ እሳት አፈ​ሰሰ።


ሄ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ጠላት ሆነ​ብኝ፤ እስ​ራ​ኤ​ልን አሰ​ጠመ። አዳ​ራ​ሾ​ች​ዋን ሁሉ ዋጠ፤ አን​ባ​ዎ​ች​ዋ​ንም አጠፋ። በይ​ሁ​ዳም ሴት ልጅ ውር​ደ​ት​ንና ጕስ​ቍ​ል​ናን አበዛ።


“ሰማይ ሆይ! ቅዱሳን ሐዋርያት ነቢያትም ሆይ! በእርስዋ ላይ ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።”


በእርስዋም ውስጥ የነቢያትና የቅዱሳን ደም በምድርም የታረዱ ሁሉ ደም ተገኘባት።


አቤቱ ጠላ​ቶ​ችህ ሁሉ እን​ዲሁ ይጥፉ፤ ወዳ​ጆ​ችህ ግን ፀሐይ በኀ​ይሉ በወጣ ጊዜ እን​ደ​ሚ​ሆን፤ እን​ዲሁ ይሁኑ። ምድ​ሪ​ቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረ​ፈች።


ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን፥ “ለምን አወ​ክ​ኸኝ? ለም​ንስ አስ​ነ​ሣ​ኸኝ?” አለው። ሳኦ​ልም መልሶ፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ይወ​ጉ​ኛ​ልና እጅግ ተጨ​ን​ቄ​አ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእኔ ርቆ​አል፤ በነ​ቢ​ያት ወይም በሕ​ልም አላ​ሚ​ዎች አል​መ​ለ​ሰ​ል​ኝም፤ ስለ​ዚ​ህም የማ​ደ​ር​ገ​ውን ታስ​ታ​ው​ቀኝ ዘንድ ጠራ​ሁህ” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቃሌ እንደ ተና​ገረ አድ​ር​ጎ​አል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥ​ት​ህን ከእ​ጅህ ነጥቆ ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ ለዳ​ዊት ሰጥ​ቶ​ታል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች