Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 28:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ሴቲ​ቱም ሳሙ​ኤ​ልን ባየች ጊዜ በታ​ላቅ ድምፅ ጮኸች፤ ሴቲ​ቱም ሳኦ​ልን፥ “አንተ ሳኦል ስት​ሆን ለምን አታ​ለ​ል​ኸኝ?” ብላ ተና​ገ​ረ​ችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሴትዮዋም ሳሙኤልን ባየችው ጊዜ በታላቅ ድምፅ ጮኸች፤ ሳኦልንም፣ “አንተ ሳኦል ሆነህ ሳለ፣ ለምን አታለልኸኝ?” አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሴትዮዋም ሳሙኤልን ባየችው ጊዜ በታልቅ ድምፅ ጮኽች፤ ሳኦልንም፥ “አንተ ሳኦል ሆነህ ሳለ፥ ለምን አታለልኸኝ?” አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እርስዋም ሳሙኤልን ባየችው ጊዜ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ በመጮኽ “ስለምን አታለልከኝ? አንተ ንጉሥ ሳኦል ነህ!” አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ሴቲቱም ሳሙኤልን ባየች ጊዜ በታላቅ ድምፅ ጮኸች፥ ሴቲቱም ሳኦልን፦ አንተ ሳኦል ስትሆን ለምን አታለልኸኝ? ብላ ተናገረችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 28:12
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በነ​ጋም ጊዜ እነሆ ልያ ነበ​ረች፤ ያዕ​ቆ​ብም ላባን፥ “ምነው እን​ደ​ዚህ አደ​ረ​ግ​ህ​ብኝ? ያገ​ለ​ገ​ል​ሁህ ስለ ራሔል አል​ነ​በ​ረ​ምን? ለምን አታ​ለ​ል​ኸኝ?” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አኪ​ያን፥ “እነሆ፥ ስለ ታመ​መው ልጅዋ ትጠ​ይ​ቅህ ዘንድ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ሚስት ትመ​ጣ​ለች፤ ራስ​ዋ​ንም ለውጣ ወደ አንተ በገ​ባች ጊዜ እን​ዲ​ህና እን​ዲህ በላት” አለው።


ሴቲ​ቱም፥ “ማንን ላስ​ነ​ሣ​ልህ?” አለ​ችው፤ እር​ሱም፥ “ሳሙ​ኤ​ልን አስ​ነ​ሽ​ልኝ” አላት።


ንጉ​ሡም፥ “አት​ፍሪ ፤ ንገ​ሪኝ፤ ማንን አየሽ?” አላት። ሴቲ​ቱም፥ “አማ​ል​ክት ከም​ድር ሲወጡ አየሁ” አለ​ችው።


ሳሙ​ኤል ግን ሞቶ ነበር፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አል​ቅ​ሰ​ው​ለት ነበር፤ በከ​ተ​ማ​ውም በአ​ር​ማ​ቴም ቀብ​ረ​ውት ነበር። ሳኦ​ልም መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን ከም​ድር አጥ​ፍቶ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች