Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 25:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 የዳ​ዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖች ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ወደ አቤ​ግያ መጡ፥ “ዳዊ​ትም ሚስት ትሆ​ኚው ዘንድ ወደ አንቺ ልኮ​ናል” ብለው ነገ​ሩ​አት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 አገልጋዮቹም ወደ ቀርሜሎስ ሄደው አቢግያን፣ “ሚስት ትሆኚው ዘንድ እንድንወስድሽ ዳዊት ወደ አንቺ ልኮናል” አሏት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 አገልጋዮቹም ወደ ቀርሜሎስ ሄደው አቢጌልን፥ “ሚስት ትሆኚው ዘንድ እንድንወስድሽ ዳዊት ወደ አንቺ ልኮናል” አሏት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 አገልጋዮቹም እርስዋ ወዳለችበት ወደ ቀርሜሎስ ሄደው “ሊያገባሽ ስለ ፈቀደ ወደ ዳዊት ልንወስድሽ መጥተናል” አሉአት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 የዳዊትም ባሪያዎች ወደ ቀርሜሎስ ወደ አቢግያ በመጡ ጊዜ፦ ዳዊት ያገባሽ ዘንድ ወደ አንቺ ልኮናል ብለው ነገሩአት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 25:40
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ርብቃ እን​ኋት፤ በፊ​ትህ ናት፤ ይዘ​ሃት ሂድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ ለጌ​ታህ ልጅ ሚስት ትሁን።”


ደግ ሴት ለባሏ ክብርን ታስገኛለች፥ ጽድቅን የምትጠላ ሴት ግን የውርደት ወንበር ናት። ሐኬተኞች ከብልጽግና ይደኸያሉ፥ ብርቱዎች ግን ብልጽግናን ይከተላሉ።


ዳዊ​ትም ናባል እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ፥ “ከና​ባል እጅ የስ​ድ​ቤን ፍርድ የፈ​ረ​ደ​ልኝ፥ ባሪ​ያ​ው​ንም ከክ​ፉ​ዎች እጅ የጠ​በቀ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የና​ባ​ልን ክፋት በራሱ ላይ መለሰ” አለ። ዳዊ​ትም ያገ​ባት ዘንድ አቤ​ግ​ያን እን​ዲ​ያ​ነ​ጋ​ግ​ሩ​ለት ላከ።


ተነ​ሥ​ታም በግ​ን​ባ​ርዋ በም​ድር ወድቃ ሰገ​ደ​ችና፥ “እነሆ፥ እኔ ገረ​ድህ የጌ​ታ​ዬን ሎሌ​ዎች እግር አጥብ ዘንድ አገ​ል​ጋይ ነኝ” አለች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች