1 ሳሙኤል 20:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)36 ብላቴናውንም፥ “ሮጠህ የምወረውራቸውን ፍላጻዎች ፈልግልኝ” አለው። ብላቴናውም በሮጠ ጊዜ ዮናታን ፍላጻውን ወደ ማዶ አሳልፎ ወረወረው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም36 ልጁንም፣ “ሩጥ! የምሰዳቸውን ፍላጻዎች ፈልጋቸው” አለው፤ ልጁም በሮጠ ጊዜ፣ ከርሱ አሳልፎ አንድ ፍላጻ ወረወረ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)36 ልጁንም፥ “ሩጥ! የምሰዳቸውን ፍላጻዎች ፈልጋቸው” አለው፤ ልጁም በሮጠ ጊዜ፥ ከእርሱ አሳልፎ አንድ ፍላጻ ወረወረ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም36 ልጁንም “ፈጥነህ ሂድና የምወረውራቸውን ፍላጻዎች ፈልገህ አምጣልኝ” አለው፤ ልጁም ሲሮጥ ዮናታን ከዚያ ልጅ ፊት አሳልፎ አንድ ፍላጻ ወረወረ፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)36 ብላቴናውንም፦ ሮጠህ የምወረውራቸውን ፍላጻዎች ፈልግልኝ አለው። ብላቴናውም በሮጠ ጊዜ ፍላጻውን ወደ ማዶ ወረወረው። ምዕራፉን ተመልከት |