1 ሳሙኤል 20:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 ከመባቻም በኋላ በማግሥቱ በሁለተኛው ቀን የዳዊት ስፍራ ባዶውን ነበረ፤ ሳኦልም ልጁን ዮናታንን፥ “የእሴይ ልጅ ትናትና ዛሬ ወደ ግብር ያልመጣ ስለምን ነው?” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም27 በማግስቱም፣ ወር በገባ በሁለተኛው ቀን የዳዊት መቀመጫ ባዶ ነበር፤ ከዚያም ሳኦል ልጁን ዮናታንን፣ “የእሴይ ልጅ ትናንትናም፣ ዛሬም ግብር ላይ ያልተገኘው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 በማግስቱም፥ ወር በገባ በሁለተኛው ቀን የዳዊት መቀመጫ ባዶ ነበር፤ ከዚያም ሳኦል ልጁን ዮናታንን፥ “የእሴይ ልጅ ትናንትናም፥ ዛሬም ግብር ላይ ያልተገኘው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 አዲስ ጨረቃ የታየችበት በዓል ካለፈ በኋላም በተከታዩ ቀን የዳዊት ወንበር ባዶ ነበር፤ ስለዚህ ሳኦል ልጁን ዮናታንን “የእሴይ ልጅ ትናንትም፥ ዛሬም ወደዚህ ግብዣ ያልመጣው ስለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 ከመባቻም በኋላ በማግሥቱ በሁለተኛው ቀን የዳዊት ስፍራ ባዶውን ነበረ፥ ሳኦልም ልጁን ዮናታንን፦ የእሴይ ልጅ ትናንትና ወይም ዛሬ ግብር ሊበላ ያልመጣ ስለ ምን ነው? አለው። ምዕራፉን ተመልከት |