Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 19:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ልብ​ሱ​ንም አወ​ለቀ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ትን​ቢት ተና​ገረ፤ ራቁ​ቱ​ንም ወድቆ በዚያ ቀን ሁሉ በዚ​ያም ሌሊት ሁሉ ተጋ​ደመ። ስለ​ዚህ፥ “ሳኦል ደግሞ ከነ​ቢ​ያት መካ​ከል ነውን?” ይባ​ባሉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እርሱም ልብሱን አውልቆ፣ በሳሙኤልም ፊት ደግሞ ትንቢት ተናገረ፤ በዚህ ሁኔታም ቀኑንና ሌሊቱን በሙሉ ዕራቍቱን ተጋደመ። ሕዝቡ፣ “ሳኦልም ደግሞ ከነቢያት እንደ አንዱ ሆኖ ተቈጠረ?” ያለው በዚህ ምክንያት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 እርሱም ልብሱን አውልቆ፥ በሳሙኤልም ፊት ደግሞ ትንቢት ተናገረ፤ በዚህ ሁኔታም ቀኑንና ሌሊቱን በሙሉ ራቁቱን ተጋደመ። ሕዝቡ፥ “ሳኦልም ደግሞ ከነቢያት እንደ አንዱ ሆኖ ተቆጠረ?” ካለው የተነሣ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ወደ ሳሙኤልም ፊት ሲቀርብ ልብሱን አውልቆ ትንቢት እየተናገረ፤ ቀኑንም ሌሊቱንም ሁሉ ራቁቱን በዚያው ተጋድሞ ዋለ፤ “ሳኦልም ከነቢያት እንደ አንዱ ሆኖ ተቈጠርን?” የሚለው የምሳሌ አነጋገር የመነጨው ከዚህ የተነሣ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ልብሱንም አወለቀ፥ በሳሙኤልም ፊት ትንቢት ተናገረ፥ ራቁቱንም ወድቆ በዚያ ቀን ሁሉ በዚያም ሌሊት ሁሉ ተጋደመ። ስለዚህ፦ ሳኦል ደግሞ ከነቢያት መካከል ነውን? ይባባሉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 19:24
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በገና ይደ​ረ​ድር ነበር፤ ዳዊ​ትም ለዐ​ይን የሚ​ያ​ን​ጸ​ባ​ርቅ የሐር ቀሚስ ለብሶ ነበር።


ዳዊ​ትም ቤተ ሰቡን ሊመ​ርቅ ተመ​ለሰ። የሳ​ኦል ልጅ ሜል​ኮ​ልም ዳዊ​ትን ለመ​ቀ​በል ወጣ​ችና ሰላ​ምታ ሰጠ​ችው፥ “ከሚ​ዘ​ፍ​ኑት አንዱ እን​ደ​ሚ​ገ​ለጥ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ሚስ​ቶች ፊት በመ​ገ​ለጡ ምንኛ የተ​ከ​በረ ነው!” አለች።


በዚያ ዓመት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ሞ​ጽን ልጅ ኢሳ​ይ​ያ​ስን፥ “ሂድ፥ ማቅ​ህን ከወ​ገ​ብህ አውጣ፤ ጫማ​ህ​ንም ከእ​ግ​ርህ አው​ልቅ፤ ያለ​ጫ​ማም በባዶ እግ​ርህ ሂድ” ብሎ ተና​ገ​ረው። እን​ዲ​ህም አደ​ረገ፤ ራቁ​ቱ​ንም ያለ ጫማ ሄደ።


ስለዚህ ነገር ዋይ ብላ ታለቅሳለች፥ ባዶ እግርዋንና ዕራቁትዋን ሆና ትሄዳለች፥ እንደ ቀበሮ ታለቅሳለች፥ እንደ ሰጐንም ዋይ ትላለች፥


“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል የሚ​ሰማ፥ ሁሉን የሚ​ችል የአ​ም​ላ​ክን ራእይ የሚ​ያይ፥ ተኝቶ ዐይ​ኖቹ የተ​ከ​ፈ​ቱ​ለት እን​ዲህ ይላል፦


የሰ​ሙ​ትም ሁሉ አደ​ነቁ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይህን ስም የሚ​ጠ​ሩ​ትን ሁሉ ይጠ​ላ​ቸው የነ​በ​ረው ይህ አይ​ደ​ለ​ምን? ስለ​ዚህ ወደ​ዚህ የመ​ጣው እያ​ሰረ ወደ ሊቀ ካህ​ናቱ ሊወ​ስ​ዳ​ቸው አይ​ደ​ለ​ምን?”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በአ​ንተ ይወ​ር​ዳል፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ትን​ቢት ትና​ገ​ራ​ለህ፤ እንደ ሌላም ሰው ሆነህ ትለ​ወ​ጣ​ለህ።


ሳሙ​ኤ​ልም እስከ ሞተ​በት ቀን ድረስ ሳኦ​ልን ለማ​የት ዳግ​መኛ አል​ሄ​ደም፤ ሳሙ​ኤ​ልም ለሳ​ኦል አለ​ቀሰ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ሳኦ​ልን ስላ​ነ​ገሠ ተጸ​ጸተ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በነ​ጋው ሳኦ​ልን ክፉ መን​ፈስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ያዘው፤ በቤ​ቱም ውስጥ ትን​ቢት ተና​ገረ። ዳዊ​ትም በየ​ቀኑ ያደ​ርግ እንደ ነበረ በእጁ በገና ይመታ ነበር። ሳኦ​ልም ጦሩን በእጁ ይዞ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች