Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 19:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ለሳ​ኦ​ልም ይህን በነ​ገ​ሩት ጊዜ ሌሎች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እነ​ር​ሱም ደግሞ ትን​ቢት ተና​ገሩ። ሳኦ​ልም እንደ ገና ሦስ​ተኛ ጊዜ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እነ​ር​ሱም ደግሞ ትን​ቢት ተና​ገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ሳኦልም ይህ በተነገረው ጊዜ ሌሎች ሰዎች ላከ፤ እነርሱም ትንቢት ተናገሩ፤ ሳኦል ለሦስተኛ ጊዜ ሰዎች ላከ፣ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ሳኦልም ይህ በተነገረው ጊዜ ሌሎች ሰዎች ላከ፤ እነርሱም ትንቢት ተናገሩ፤ ሳኦል ለሦስተኛ ጊዜ ሰዎች ላከ፥ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሳኦል ይህን በሰማ ጊዜ ሌሎች መልእክተኞችን ላከ፤ እነርሱም እንደዚያው ትንቢት መናገር ቀጠሉ፤ ሳኦልም ለሦስተኛ ጊዜ ሌሎች መልእክተኞችን ቢልክ ያው ነገር በእነርሱም ላይ ተደገመ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ሳኦልም ያንን በሰማ ጊዜ ሌሎች መልእክተኞችን ሰደደ፥ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ። ሳኦልም እንደ ገና ሦስተኛ ጊዜ መልእክተኞችን ሰደደ፥ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 19:21
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በውኑ ኢት​ዮ​ጵ​ያዊ መል​ኩን ወይስ ነብር ዝን​ጕ​ር​ጕ​ር​ነ​ቱን ይለ​ውጥ ዘንድ ይች​ላ​ልን? በዚያ ጊዜ ክፋ​ትን የለ​መ​ዳ​ችሁ እና​ንተ ደግሞ በጎ ለማ​ድ​ረግ ትች​ላ​ላ​ች​ሁን?


“ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ መን​ፈ​ሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈ​ስ​ሳ​ለሁ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም ትን​ቢ​ትን ይና​ገ​ራሉ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ሕል​ምን ያል​ማሉ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ች​ሁም ራእ​ይን ያያሉ፤


ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ያመ​ጡት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ የነ​ቢ​ያ​ት​ንም ጉባኤ አገኙ፤ ሳሙ​ኤ​ልም አለ​ቃ​ቸው ሆኖ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቆሞ ነበረ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በሳ​ኦል መል​እ​ክ​ተ​ኞች ላይ ወረደ፤ እነ​ር​ሱም ትን​ቢት ይና​ገሩ ጀመር።


ሳኦ​ልም እጅግ ተቈጣ፤ እር​ሱም ደግሞ ወደ አር​ማ​ቴም መጣ፤ በመ​ሴ​ፋም አው​ድማ ወዳ​ለው ወደ ታላቁ የውኃ ጕድ​ጓድ ደረሰ። “ሳሙ​ኤ​ልና ዳዊት የት ናቸው?” ብሎ ጠየቀ፤ “እነሆ፥ በአ​ው​ቴ​ዘ​ራማ ናቸው” አሉት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች