Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 17:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 በኋ​ላ​ውም እከ​ተ​ለ​ውና እመ​ታው ነበር። ከአ​ፉም አስ​ጥ​ለው ነበር፤ በተ​ነ​ሣ​ብ​ኝም ጊዜ ጕሮ​ሮ​ውን አንቄ እመ​ታ​ውና እገ​ድ​ለው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ተከትዬ በመሄድ እመታውና ከአፉ አስጥል ነበር፤ ፊቱን ወደ እኔ በሚያዞርበትም ጊዜ ጕረሮውን ይዤ በመምታት እገድለው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ተከትዬ በመሄድ እመታውና ከአፉ አስጥል ነበር፤ ፊቱን ወደ እኔ በሚያዞርበትም ጊዜ ጉሮሮውን ይዤ በመምታት እገድለው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ተከትዬው ሄጄ አደጋ በመጣል የወሰደውን ጠቦት አስጥለው ነበር፤ አንበሳው ወይም ድቡ ወደ እኔ ተመልሶ በሚመጣበትም ጊዜ ጉሮሮውን አንቄ በመምታት እገድለው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 በኋላውም እከተለውና እመታው ነበር፥ ከአፉም አስጥለው ነበር፥ በተነሣብኝም ጊዜ ጉሮሮውን ይዤ እመታውና እገድለው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 17:35
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በቀ​በ​ስ​ሄል የነ​በ​ረው ታላቅ ሥራ ያደ​ረ​ገው የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ የሞ​ዓ​ባ​ዊ​ውን የአ​ር​ኤ​ልን ሁለት ልጆች ገደለ፤ በአ​መ​ዳ​ዩም ወራት ወርዶ በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ አን​በሳ ገደለ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ የተ​ተ​ከሉ ናቸው፥ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም አደ​ባ​ባይ ውስጥ ይበ​ቅ​ላሉ።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እረኛ ከአ​ን​በሳ አፍ ሁለት እግ​ርን ወይም የጆ​ሮን ጫፍ እን​ደ​ሚ​ያ​ድን፥ እን​ዲሁ በሰ​ማ​ርያ በአ​ሕ​ዛብ ፊትና በደ​ማ​ስቆ የተ​ቀ​መ​ጡት የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ይድ​ናሉ።


ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን አለው፥ “እኔ ባሪ​ያህ የአ​ባ​ቴን በጎች ስጠ​ብቅ አን​በሳ ወይም ድብ ይመጣ ነበር፤ ከመ​ን​ጋ​ውም ጠቦት ይወ​ስድ ነበር።


እኔ ባሪ​ያህ አን​በ​ሳና ድብ ገደ​ልሁ፤ ይህም ያል​ተ​ገ​ረ​ዘው ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ ከእ​ነ​ርሱ እንደ አንዱ ይሆ​ናል። እን​ግ​ዲህ እገ​ድ​ለው ዘንድ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተግ​ዳ​ሮ​ትን አስ​ወ​ግድ ዘንድ ዛሬ አል​ሄ​ድ​ምን? የሕ​ያው አም​ላክ ጭፍ​ሮ​ችን ይገ​ዳ​ደር ዘንድ ይህ ቈላፍ ምን​ድን ነው?”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች