Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 12:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ባት​ሰሙ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ላይ ብታ​ምፁ፥ በእ​ና​ን​ተና በን​ጉ​ሣ​ችሁ ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ትመ​ጣ​ለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እግዚአብሔርን የማትታዘዙና በትእዛዞቹም ላይ የምታምፁ ከሆነ ግን፣ እጁ በአባቶቻችሁ ላይ እንደ ነበረች ሁሉ በእናንተም ላይ ትሆናለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ጌታን የማትሰሙና የማትታዘዙ፥ በትእዛዛቱም ላይ የምታምጹ ከሆነ ግን፥ እጁ በአባቶቻችሁ ላይ እንደ ነበረች ሁሉ በእናንተም ላይ ትሆናለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል ባታዳምጡ፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ላይ ብታምፁ በእናንተና በንጉሣችሁ ላይ የእግዚአብሔር ቅጣት ይበረታባችኋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል ባትሰሙ፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ላይ ብታምፁ፥ በእናንተና በንጉሣችሁ ላይ የእግዚአብሔር እጅ ትሆናለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 12:15
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እር​ሱም ንጉ​ሡን አሳን፥ የይ​ሁ​ዳ​ንና የብ​ን​ያ​ምን ሕዝብ ሁሉ ሊገ​ናኝ ወጣ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አሳ ይሁ​ዳና ብን​ያም ሁሉ ሆይ፥ ስሙኝ፤ እና​ንተ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ብት​ሆኑ እርሱ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሆ​ናል፤ ብት​ፈ​ል​ጉ​ትም ይገ​ኝ​ላ​ች​ኋል፤ ብት​ተ​ዉት ግን ይተ​ዋ​ች​ኋል።


እንቢ ብት​ሉና ባት​ሰ​ሙኝ ግን ሰይፍ ትበ​ላ​ች​ኋ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ ይህን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


እንደ እጁ ሥራ ፍዳው ይደ​ረ​ግ​በ​ታ​ልና ለበ​ደ​ለኛ ወዮ! ክፉም ይደ​ር​ስ​በ​ታል።


ጻዴ። ቃሉን አማ​ር​ሬ​አ​ለ​ሁና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድቅ ነው። እና​ንተ አሕ​ዛብ ሁሉ እባ​ካ​ችሁ ስሙ፤ መከ​ራ​ዬ​ንም ተመ​ል​ከቱ፤ ደና​ግ​ሎ​ችና ጐል​ማ​ሶች ተማ​ር​ከው ሄደ​ዋ​ልና።


እኔ ዐመ​ፃ​ች​ሁ​ንና የአ​ን​ገ​ታ​ች​ሁን ድን​ዳኔ አው​ቃ​ለ​ሁና፤ እኔም ዛሬ ከእ​ና​ንተ ጋር ገና በሕ​ይ​ወት ሳለሁ እና​ንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዐም​ፃ​ች​ኋል፤ ይል​ቁ​ንስ ከሞ​ትሁ በኋላ እን​ዴት ይሆ​ናል?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትታ​ችሁ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ብታ​መ​ልኩ፥ መል​ካ​ምን ባደ​ረ​ገ​ላ​ችሁ ፋንታ ተመ​ልሶ ክፉ ነገር ያደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋል፤ ያጠ​ፋ​ች​ሁ​ማል” አላ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ነ​ርሱ ላይ እንደ ማለ፥ ወደ ወጡ​በት ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ትከ​ፋ​ባ​ቸው ነበ​ረች፤ እጅ​ግም ተጨ​ነቁ።


አም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረሱ፤ ለአ​ሶር ሠራ​ዊ​ትም አለቃ ለሲ​ሣራ እጅ፥ ለፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እጅ፥ ለሞ​ዓ​ብም ንጉሥ እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ወጉ​አ​ቸው፤


ከሄ​ደ​ችም በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በከ​ተ​ማ​ዪቱ ላይ መጣች፤ ታላቅ ሁከ​ትም ሆነ፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ሰዎች ታላ​ቁ​ንም ታና​ሹ​ንም መታ፤ የው​ስጥ አካ​ላ​ቸ​ው​ንም በእ​ባጭ መታ​ቸው፤ የጌት ሰዎ​ችም የው​ስጥ አካ​ላ​ቸ​ውን ምስል ሠሩ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች