Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ቆሮንቶስ 3:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በሥ​ጋዊ ሕግም ትኖ​ራ​ላ​ች​ሁና እርስ በር​ሳ​ችሁ የም​ት​ቃ​ኑና የም​ት​ከ​ራ​ከሩ ከሆነ ግን ሥጋ​ው​ያን መሆ​ና​ችሁ አይ​ደ​ለ​ምን? እንደ ሰው ልማ​ድስ የም​ት​ኖሩ መሆ​ና​ችሁ አይ​ደ​ለ​ምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 አሁንም ሥጋውያን ናችሁ፤ በመካከላችሁ ቅናትና ክርክር አለ። ታዲያ፣ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን? ተግባራችሁስ እንደ ማንኛውም ሰው ተግባር መሆኑ አይደለምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እናንተ ገና ሥጋውያን ናችሁ፤ ቅናትና ጭቅጭቅ እስከተገኘባችሁ፥ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እናንተ አሁንም ገና ሥጋውያን ናችሁ፤ እርስ በርሳችሁ ስለምትቀናኑና ስለምትከራከሩ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን? የምትሠሩትስ እንደ ተራ ሰው አይደለምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ገና ሥጋውያን ናችሁና እስከ አሁን ድረስ ገና አትችሉም። ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ቆሮንቶስ 3:3
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነ​ርሱ ግን ቃል ኪዳ​ንን እን​ደ​ሚ​ያ​ፈ​ርስ ሰው ሆኑ፤ በዚ​ያም ላይ ከዱኝ።


በቀን እን​ደ​ሚ​ሆን በጽ​ድቅ ሥራ እን​መ​ላ​ለስ፤ በዘ​ፈ​ንና በስ​ካር፥ በዝ​ሙ​ትና በመ​ዳ​ራ​ትም አይ​ሁን፤ በክ​ር​ክ​ርና በቅ​ና​ትም አይ​ሁን።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን! አንድ ቃል እን​ድ​ት​ና​ገሩ፥ እን​ዳ​ታ​ዝኑ፥ ፍጹ​ማ​ንም እን​ድ​ት​ሆኑ፥ ሁላ​ች​ሁ​ንም፦ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፤ እን​ዳ​ት​ለ​ያ​ዩም አንድ ልብና አንድ አሳብ ሆና​ችሁ ኑሩ።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ! እን​ደ​ም​ት​ጣ​ሉና እን​ደ​ም​ት​ከ​ራ​ከሩ ከቀ​ሎ​ኤስ ወገ​ኖች ስለ እና​ንተ ነገ​ሩኝ።


ከሁሉ አስ​ቀ​ድሞ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በም​ት​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ እን​ደ​ም​ት​ጣ​ሉና እን​ደ​ም​ት​ከ​ራ​ከሩ ሰም​ቻ​ለሁ፤ የማ​ም​ነ​ውም አለኝ።


ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ፥ “እኔ የጳ​ው​ሎስ ነኝ” የሚል አለና፤ ሌላ​ውም፥ “እኔ የአ​ጵ​ሎስ ነኝ” ቢል እና​ንተ ሥጋ​ው​ያን መሆ​ና​ችሁ አይ​ደ​ለ​ምን?


ነገር ግን ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ እን​ደ​ም​ወ​ደው ሆና​ችሁ ያላ​ገ​ኘ​ኋ​ችሁ እንደ ሆነ፤ እኔም እን​ደ​ማ​ት​ወ​ዱት እሆ​ን​ባ​ች​ኋ​ለሁ ብዬ እፈ​ራ​ለሁ፤ ወይም እኮ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ክር​ክር፥ ኵራት፥ መቀ​ና​ናት፥ መበ​ሳ​ጨት፥ መዘ​ባ​በት፥ ወይም መተ​ማ​ማት፥ መታ​ወክ፥ ወይም ልብን ማስ​ታ​በይ ይኖር ይሆ​ናል።


እርስ በር​ሳ​ችሁ የም​ት​በ​ላ​ሉና የም​ት​ነ​ካ​ከሱ ከሆነ ግን፥ እርስ በር​ሳ​ችሁ እን​ዳ​ት​ተ​ላ​ለቁ ተጠ​ን​ቀቁ።


እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።


ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ አሉና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች