Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ቆሮንቶስ 3:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ወድ​ሞች ሆይ፥ እኔስ የሥ​ጋና የደም እንደ መሆ​ና​ችሁ፥ ክር​ስ​ቶ​ስ​ንም በማ​መን ሕፃ​ናት እንደ መሆ​ና​ችሁ እንጂ እንደ መን​ፈ​ሳ​ው​ያን ላስ​ተ​ም​ራ​ችሁ አል​ቻ​ል​ሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ወንድሞች ሆይ፤ በክርስቶስ ገና ሕፃናት እንደ መሆናችሁ፣ እንደ ሥጋውያን እንጂ እንደ መንፈሳውያን ልናገራችሁ አልቻልሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ወንድሞች ሆይ! እኔም፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ወንድሞቼ ሆይ! እኔ ሳስተምራችሁ ሥጋውያንና በክርስቶስ ገና ያልጠነከራችሁ ሕፃናት እንደ መሆናችሁ መጠን ነው እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ መጠን አይደለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ቆሮንቶስ 3:1
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን “ወደ ኋላዬ ሂድ፤ አንተ ሰይጣን! የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና፥ ዕንቅፋት ሆነህብኛል፤” አለው።


የኦ​ሪት ሕግ መን​ፈ​ሳዊ እንደ ሆነ እና​ው​ቃ​ለን፤ እኔ ግን ለኀ​ጢ​አት የተ​ሸ​ጥሁ ሥጋዊ ነኝ።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በአ​እ​ምሮ እንደ ሕፃ​ናት አት​ሁኑ፤ ነገር ግን ለክፉ ነገር እንደ ሕፃ​ናት ሁኑ፤ በዕ​ው​ቀ​ትም ፍጹ​ማን ሁኑ።


ራሱን እንደ ነቢይ አድ​ርጎ ወይም መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዳ​ደ​ረ​በት አድ​ርጎ የሚ​ቈ​ጥር ቢኖር፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ነውና ይህን የጻ​ፍ​ሁ​ላ​ች​ሁን ይወቅ።


ለዐ​ዋ​ቆች ጥበ​ብን እን​ነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለን፤ ነገር ግን የዚ​ህን ዓለም ጥበብ ወይም ያልፉ ዘንድ ያላ​ቸ​ውን የዚ​ህን ዓለም ሹሞች ጥበብ አይ​ደ​ለም።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ከእ​ና​ንተ ወገን የተ​ሳ​ሳተ ሰው ቢኖር በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የጸ​ና​ችሁ እና​ንት እን​ዳ​ት​ሳ​ሳቱ ለራ​ሳ​ችሁ እየ​ተ​ጠ​በ​ቃ​ችሁ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ሰው ቅን​ነት ባለው ልቡና አጽ​ኑት።


ወተ​ትን የሚ​ጋት ሁሉ ሕፃን ስለ​ሆነ፥ የጽ​ድ​ቅን ቃል ሊያ​ውቅ አይ​ሻም።


ልጆች ሆይ፥ ኃጢአታችሁ ስለ ስሙ ተሰርዮላችኋልና እጽፍላችኋለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች