ሮሜ 16:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም17 ወንድሞች ሆይ፤ መለያየትን ከሚፈጥሩትና የተማራችሁትን ትምህርት በመቃወም በጕዟችሁ መሰናክል ከሚያደርጉት እንድትጠነቀቁ አሳስባችኋለሁ፤ ከእነርሱም ራቁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ወንድሞች ሆይ! ከሚለያዩትና እናንተ የተማራችሁትን ትምህርት በመቃወም መሰናክል ከሚያደርጉ ሰዎች እንድትጠነቀቁ አሳስባችኋለሁ፤ ከእነርሱም ራቁ፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ወንድሞች ሆይ! ለተቀበላችሁት ትምህርት ተቃዋሚዎች በመሆን በመካከላችሁ መከፋፈልንና ችግርን ከሚያመጡ ሰዎች ተጠንቀቁ፤ ከእነርሱም ራቁ! ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ወንድሞቻችን ሆይ፥ እናንተ የተማራችሁትን ትምህርት የሚቃወሙትን፥ መለያየትንና ማሰናከያን የሚያደርጉትን እንድታውቁባቸው እማልዳችኋለሁ፤ ከእነርሱም ተለዩ፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ የተማራችሁትን ትምህርት የሚቃወሙትን መለያየትንና ማሰናከያን የሚያደርጉትን ሰዎች እንድትመለከቱ እለምናችኋለሁ፥ ከእነርሱ ዘንድ ፈቀቅ በሉ፤ ምዕራፉን ተመልከት |