Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 89:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ምሕረትህን ለዘላለም እንደምትመሠርት፣ ታማኝነትህንም በሰማይ እንደምታጸና እናገራለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህን ለዘለዓለም እዘምራለሁ፥ እውነትህንም በአፌ ለልጅ ልጅ እናገራለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ፍቅርህ ለዘለዓለም እንደሚጸናና ታማኝነትህን እንደ ሰማይ እንደሚመሠረት እናገራለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ተራ​ሮች ሳይ​ወ​ለዱ፥ ምድ​ርም ዓለ​ምም ሳይ​ሠሩ፥ ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ መቼም መች አንተ ነህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 89:2
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚያም እንዲህ አልሁ፤ “ለሚወድዱህና ትእዛዝህን ለሚያከብሩ የፍቅርህን ቃል ኪዳን የምትጠብቅ ታላቅና የተፈራህ አምላክ፣ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤


ለመስማት አልፈለጉም፤ በመካከላቸውም ያደረግሃቸውን ታምራት ማስታወስ አልቻሉም። ዐንገታቸውን አደነደኑ፤ በዐመፃቸውም ወደ ባርነታቸው ለመመለስ መሪ ሾሙ። አንተ ግን ይቅር ባይ አምላክ፣ ቸርና ርኅሩኅ፣ ለቍጣም የዘገየህና ምሕረትህ የበዛ ነህ። ስለዚህ አልተውሃቸውም፤


አንተ ግን ቸርና መሓሪ አምላክ ነህና ከምሕረትህ ብዛት የተነሣ፣ ፈጽመህ አላጠፋሃቸውም፤ አልተውሃቸውምም።


የእግዚአብሔር ምሕረት ግን፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚፈሩት ላይ ነው፤ ጽድቁም እስከ ልጅ ልጅ ድረስ በላያቸው ይሆናል፤


እግዚአብሔር ሆይ፤ ቃልህ በሰማይ፣ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።


እርሱ ሰማይንና ምድርን፣ ባሕርንም፣ በውስጣቸውም የሚኖሩትን ሁሉ የፈጠረ፣ ታማኝነቱም ለዘላለም የሆነ ነው፤


እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ እስከ ሰማያት ይደርሳል፤ ታማኝነትህም እስከ ጠፈር ይመጥቃል።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህን አትንፈገኝ፤ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ፤


ዋላ የምንጭ ውሃ እንደምትናፍቅ፣ አምላክ ሆይ፤ ነፍሴም እንዲሁ አንተን ትናፍቃለች።


በሰማይ ታማኝ ምስክር ሆና እንደምትኖረው፣ እንደ ጨረቃ እርሱ ለዘላለም ይመሠረታል።” ሴላ


እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰማያት ድንቅ ሥራህን፣ ታማኝነትህንም በቅዱሳን ጉባኤ መካከል ያወድሳሉ፤


ይዋሽ ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፤ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም፤ ተናግሮ አያደርገውምን? ተስፋ ሰጥቶስ አይፈጽመውምን?


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈጽሞ አያልፍም።


ምሕረቱም ለሚፈሩት ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።


እግዚአብሔር ከቶ ሊዋሽ አይችልም፤ እርሱ በሁለት በማይለወጡ ነገሮች በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ወደ እርሱ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንድናገኝ አድርጓል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች