Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 86:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ወደ እኔ ተመልከት፤ ማረኝም፤ ለባሪያህ ኀይልህን ስጥ፤ የሴት ባሪያህንም ልጅ አድን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ወደ እኔ ተመልከት፥ ራራልኝ፥ ኃይልህን ለአገልጋይህ፥ ማዳንህንም ለአግልጋይቱ ልጅ ለእኔ ስጥ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ወደ እኔ ተመልሰህ ራራልኝ፤ ለእኔ ለአገልጋይህ ብርታትን ስጠኝ፤ እኔን የሴት አገልጋይህን ልጅ አድነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 86:16
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ በእውነት ባሪያህ ነኝ፤ እኔ የሴት ባሪያህ ልጅ፣ ባሪያህ ነኝ፤ ከእስራቴም ፈታኸኝ።


ስምህን ለሚወድዱ ማድረግ ልማድህ እንደ ሆነ ሁሉ፣ ወደ እኔ ተመልሰህ ምሕረት አድርግልኝ።


እኔ የአንተ ነኝ፤ እባክህ አድነኝ፤ ሕግህንም ፈልጌአለሁና።


በጠራሁህ ቀን መልስ ሰጠኸኝ፤ ነፍሴን በማደፋፈርም ብርቱ አደረግኸኝ።


እኔ ብቸኛና የተጨነቅሁ እንደ መሆኔ፣ ወደ እኔ ተመለስ፤ ምሕረትም አድርግልኝ።


ጠላቶቼ በክፋት በመናገር፣ “የሚሞተው መቼ ነው? ስሙስ የሚደመሰሰው ምን ቀን ነው?” ይላሉ።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ በጎ ናትና ስማኝ፤ እንደ ርኅራኄም ብዛት መለስ በልልኝ።


ብፁዓን ናቸው፤ አንተን ብርታታቸው ያደረጉ፣ በልባቸው የጽዮንን መንገድ የሚያስቡ፤


እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል? ለአገልጋዮችህም ራራላቸው።


ስለ እኔም ሲናገሩ፣ ‘ጽድቅና ኀይል፣ በእግዚአብሔር ብቻ ነው’ ይላሉ።” በርሱ ላይ በቍጣ የተነሡ ሁሉ፣ ወደ እርሱ መጥተው ያፍራሉ።


በእግዚአብሔር አበረታቸዋለሁ፤ በስሙም ይመላለሳሉ” ይላል እግዚአብሔር።


ማርያምም፣ “እነሆ፤ እኔ የጌታ ባሪያ ነኝ፤ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ” አለች። ከዚያም መልአኩ ተለይቷት ሄደ።


በውስጥ ሰውነታችሁ እንድትጠነክሩ፣ ከክብሩ ባለጠግነት በመንፈሱ በኩል ኀይል እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ፤


በተረፈ በጌታና ብርቱ በሆነው ኀይሉ ጠንክሩ።


ኀይልን በሚሰጠኝ በርሱ ሁሉን ማድረግ እችላለሁ።


ታላቅ ጽናትና ትዕግሥት ይኖራችሁ ዘንድ፣ እንደ ክቡር ጕልበቱ መጠን በኀይል ሁሉ እየበረታችሁ፣ ደስ እየተሰኛችሁ፣


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች