Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 2:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 አሕዛብ ለምን በቍጣ ተነሣሡ? ሕዝቡስ ለምን በከንቱ አሤሩ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 አሕዛብ ለምን ያጉረመርማሉ? ለምንስ ከንቱዉን ያሰላስላሉ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 አሕዛብ ስለምን ያሤራሉ? ሕዝቦችስ ለምን በከንቱ ያድማሉ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አሕ​ዛብ ለምን ዶለቱ? ወገ​ኖ​ችስ ለምን ከንቱ ይና​ገ​ራሉ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 2:1
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ አደቀቅኋቸው፤ እንደ መንገድ ላይ ጭቃም ረገጥኋቸው።


ክፋት ቢያስቡብህ፣ ተንኰል ቢወጥኑብህም አይሳካላቸውም፤


ሕዝቦች በዐመፅ ተነሡ፤ መንግሥታትም ወደቁ፤ ድምፁን ከፍ አድርጎ አሰማ፤ ምድርም ቀለጠች።


የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው፤ የያዕቆብም አምላክ መጠጊያችን ነው። ሴላ


ጌታ ሆይ፤ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ፤ በሰዎችም መካከል እዘምርልሃለሁ፤


የባላጋራዎችህን ድንፋታ፣ ዘወትር የሚነሣውን የጠላቶችህን ፉከራ አትርሳ።


በሕዝብህ ላይ በተንኰል አሤሩ፤ በውድ ልጆችህ ላይ በአንድነት ተመካከሩ።


እናንተ አሕዛብ፣ ፎክሩ፤ ነገር ግን ደንግጡ! በሩቅ አገር ያላችሁ አድምጡ። ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤ ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤


“ነገር ግን ገበሬዎቹ ልጁን ባዩት ጊዜ፣ ‘ይህማ ወራሹ ነው፤ ኑ፣ እንግደለውና ርስቱን እንውረስ’ ተባባሉ።


ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤ እነርሱም ያፌዙበታል፤ ያንገላቱታል፤ ይተፉበታል፤ ይገርፉታል፤ ከዚያም ይገድሉታል።


እነርሱም በዚህ ደስ አላቸው፣ ገንዘብ ሊሰጡትም ተዋዋሉ።


ሕዝቡም ተባብረው በጳውሎስና በሲላስ ላይ ተነሡባቸው፤ ገዦቹም ልብሳቸው ተገፍፎ በበትር እንዲደበደቡ አዘዙ።


ሰዎቹም ይህን በሰሙ ጊዜ ክፉኛ ተቈጡ፤ ሊገድሏቸውም ፈለጉ።


እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉ ግን ድል ይነሣቸዋል፤ ምክንያቱም እርሱ የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ነው፤ ከርሱ ጋራ ያሉ የተጠሩት፣ የተመረጡትና የታመኑትም ዐብረው ድል ይነሣሉ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች