Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 125:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እግዚአብሔር ሆይ፤ መልካም ለሆኑ፣ ልባቸውም ለቀና መልካም አድርግ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 አቤቱ፥ ለመልካሞች፥ ልባቸውም ለቀና መልካምን አድርግ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እግዚአብሔር ሆይ! ትእዛዞችህን ለሚፈጽሙ ደጋግ ሰዎች ቸርነት አድርግላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 አቤቱ፥ በአ​ዜብ እን​ዳሉ ፈሳ​ሾች ምር​ኮ​አ​ች​ንን መልስ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 125:4
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንተ መልካም ነህ፤ የምታደርገው መልካም ነው፤ እንግዲህ ሥርዐትህን አስተምረኝ።


እኔ እንዳላፍር፣ ልቤ በሥርዐትህ ፍጹም ይሁን።


ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔር ኀጢአቱን የማይቈጥርበት፣ በመንፈሱም ሽንገላ የሌለበት፤


ለሚያውቁህ ምሕረትህ፣ ልባቸውም ለቀና ጽድቅህ ዘወትር አይቋረጥባቸው።


በበጎ ፈቃድህ ጽዮንን አበልጽጋት፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጥሮች ሥራ።


ጋሻዬ ልዑል አምላክ ነው፤ እርሱ ልበ ቅኖችን ያድናቸዋል።


እግዚአብሔር ልባቸው ንጹሕ ለሆነ፣ ለእስራኤል እንዴት ቸር ነው!


እግዚአብሔር አምላክ ፀሓይና ጋሻ ነውና፤ እግዚአብሔር ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር ያለ ነቀፋ የሚሄዱትን፣ መልካም ነገር አይነፍጋቸውም።


የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ በአንተ የታመነ ሰው ብፁዕ ነው።


ፍርድ ተመልሶ በጽድቅ አሠራር ላይ ይመሠረታል፤ ልባቸውም ቀና የሆነ ሁሉ ይከተሉታል።


እርሱን ተስፋ ለሚያደርጉት፣ ለሚፈልገውም ሰው እግዚአብሔር መልካም ነው።


ኢየሱስም፣ ናትናኤል ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ፣ “እነሆ፤ ተንኰል የሌለበት እውነተኛ እስራኤላዊ” አለ።


እግዚአብሔር ዐመፀኛ አይደለም፤ እርሱ ሥራችሁን እንዲሁም በፊትም ሆነ አሁን ቅዱሳንን በመርዳት ስለ ስሙ ያሳያችሁትን ፍቅር አይረሳም።


በአፋቸው ምንም ዐይነት ውሸት አልተገኘም፤ ነቀፋም የለባቸውም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች