Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 8:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ፤ በፍትሕም ጐዳና እጓዛለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ፥ በፍርድም ጎዳና መካከል፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 የእኔ መንገድ የጽድቅ መንገድ ነው፤ እኔ የምከተለው የፍትሕን ፈለግ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ፥ በፍርድ ጎዳና መካከልም እመላለሳለሁ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 8:20
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነፍሴንም ይመልሳታል። ስለ ስሙም፣ በጽድቅ መንገድ ይመራኛል።


አስተምርሃለሁ፤ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤ እመክርሃለሁ፤ በዐይኔም እከታተልሃለሁ።


አንተም በደጋግ ሰዎች ጐዳና ትሄዳለህ፤ የጻድቃንንም መንገድ ይዘህ ትጓዛለህ።


በዚያ ጊዜ ጽድቅን፣ ፍትሕን፣ ሚዛናዊነትን፣ መልካሙንም መንገድ ሁሉ ትገነዘባለህ፤


በመንገድህ ሁሉ እርሱን ዕወቅ፤ እርሱም ጐዳናህን ቀና ያደርገዋል።


በምትሄድበት ሁሉ ይመሩሃል፤ በምትተኛበት ጊዜ ይጠብቁሃል፤ በምትነቃበት ጊዜም ያነጋግሩሃል።


ፍሬዬ ከንጹሕ ወርቅ ይበልጣል፤ ስጦታዬም ከነጠረ ብር።


ለሚወድዱኝ ብልጽግና እሰጣለሁ፤ ግምጃ ቤታቸውንም እሞላለሁ።


ብዙ አሕዛብ መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ በጐዳናውም እንድንሄድ፤ መንገዱን ያስተምረናል።” ሕግ ከጽዮን፣ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።


አይራቡም፤ አይጠሙም፤ የምድረ በዳ ትኵሳት ወይም የፀሓይ ቃጠሎ አይጐዳቸውም። የሚራራላቸው ይመራቸዋል፤ በውሃ ምንጭ ዳርም ያሰማራቸዋል።


እነሆ፤ እርሱን ለሕዝቦች ምስክር፣ መሪ፣ የጦር አዝማችም አድርጌዋለሁ።


በር ጠባቂው በሩን ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰማሉ። የራሱንም በጎች በየስማቸው እየጠራ ያወጣቸዋል።


እንግዲህ አምላካችሁ እግዚአብሔር ያዘዛችሁን ለመፈጸም ተጠንቀቁ፤ ቀኝም ግራም አትበሉ።


ምክንያቱም በዙፋኑ መካከል ያለው በግ እረኛቸው ይሆናል፤ ወደ ሕይወት ውሃ ምንጭም ይመራቸዋል፤ እግዚአብሔር እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች