Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 21:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 እግዚአብሔርን ለመቋቋም የሚያስችል፣ አንዳችም ጥበብ፣ ማስተዋልና ዕቅድ የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ያለ ጌታ የሚሠምር፥ ጥበብም የለም፥ ማስተዋልም የለም፥ ምክርም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ሰው በጥበቡ፥ በአስተዋይነቱና በዕቅዱ በእግዚአብሔር ላይ መነሣት አይችልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ጥበብና ብርታት፥ ምክርም፥ በኃጥእ ዘንድ የሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 21:30
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን ኦርዮ ከጌታው አገልጋዮች ሁሉ ጋራ በንጉሡ ቤት ቅጽር በር ተኛ እንጂ፣ ወደ ቤቱ አልወረደም ነበር።


አኪያም የእግሯን ኮቴ ድምፅ እበሩ ላይ እንደ ሰማ እንዲህ አላት፤ “የኢዮርብዓም ሚስት ሆይ ግቢ፤ ግን ለምንድን ነው ሌላ ሴት መስለሽ ለመታየት የፈለግሽው? ለአንቺ ከባድ ነገር እንድነግርሽ ተልኬአለሁ።


ከጦር አለቆቹም አንዱ፣ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ ከእኛ በኩል ማንም ሰው የለም፤ ነገር ግን አንተ በእልፍኝህ ሆነህ እንኳ የምትናገረውን አንዲቱም ሳትቀር ለእስራኤል ንጉሥ የሚነግረው በእስራኤል ያለው ነቢዩ ኤልሳዕ ነው” አለው።


መሰነጊያ በአፍንጫው ልታስገባ፣ ወይም ጕንጩን በሜንጦ ልትበሳ ትችላለህን?


በሰው ልብ ብዙ ሐሳብ አለ፤ የሚፈጸመው ግን የእግዚአብሔር ሐሳብ ነው።


አሁን ያለው ሁሉ አስቀድሞ ስም የተሰጠው ነው፤ ሰው የሚሆነውም አስቀድሞ የታወቀ ነው፤ ከራሱ ይልቅ ከሚበረታ ጋራ፣ ማንም አይታገልም።


የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አስቧል፤ ማንስ ያግደዋል? እጁም ተዘርግቷል? ማንስ ይመልሰዋል?


የጦር ስልትና ኀይል አለኝ ትላለህ፤ ነገር ግን ባዶ ቃል ብቻ ትናገራለህ። በእኔ ላይ ያመፅኸው በማን ተደግፈህ ነው?


“ከዐፈር ሸክላዎች መካከል፣ ከሠሪው ጋራ ክርክር ለሚገጥም ወዮለት! ጭቃ፣ ሸክላ ሠሪውን፣ ‘ምን እየሠራህ ነው?’ ይለዋልን? የምትሠራውስ ሥራ፣ ‘እጅ የለህም’ ይልሃልን?


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጥበበኛ በጥበቡ አይታበይ፤ ኀያልም በኀይሉ አይመካ፤ ሀብታምም በሀብቱ አይኵራራ፤


ሰዎቹ ግን ባላቸው ኀይል እየቀዘፉ ወደ የብስ ለመጠጋት ሞከሩ፤ ይሁን እንጂ አልቻሉም፤ ባሕሩ የባሰ ይናወጥ ነበርና።


ስለዚህ አሁንም የምላችሁ፦ እነዚህን ሰዎች ተዉአቸው! አትንኳቸው! ሐሳባቸው ወይም አድራጎታቸው ከሰው ከሆነ ይጠፋልና፤


ከእግዚአብሔር ከሆነ ግን ልትገቷቸው አትችሉም፤ እንዲያውም ከእግዚአብሔር ጋራ ስትጣሉ ትገኙ ይሆናል።”


ለኢያሪኮም ንጉሥ፣ “እነሆ፤ ምድሪቱን ሊሰልሉ ጥቂት እስራኤላውያን በሌሊት ወደዚህ መጥተዋል” ተብሎ ተነገረው።


ደግሞም፣ “የሚያደናቅፍ፣ የሚጥላቸውም ዐለት ሆነ።” የሚደናቀፉትም ቃሉን ባለመታዘዛቸው ነው፤ የተመደቡት ለዚህ ነውና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች