ሉቃስ 12:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም1 በዚያ ጊዜ፣ በብዙ ሺሕ የሚቈጠር ሕዝብ እርስ በርስ እስኪረጋገጥ ድረስ ተሰብስቦ ሳለ፣ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር፤ “ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠንቀቁ፤ ይህም ግብዝነት ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 በዚያን ጊዜ፥ በሺዎች የሚቈጠሩ ሰዎች ተሰብስበው ከብዛታቸው የተነሣ እየተረጋገጡ ሳለ፥ በቅድሚያ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር፦ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠንቀቁ፤ እርሱም ግብዝነት ነው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 በዚያን ጊዜ በብዙ ሺህ የሚቈጠሩ ሰዎች ተሰበሰቡ፤ ከብዛታቸውም የተነሣ እርስ በርሳቸው እየተጋፉ ይረጋገጡ ነበር፤ ኢየሱስም በቅድሚያ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር፤ “ከፈሪሳውያን እርሾ ማለትም ከግብዝነታቸው ተጠንቀቁ ማለት ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 በዚያን ጊዜም እጅግ ብዙ ሰዎች እርስ በርሳቸው እስኪረጋገጡ ድረስ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ደቀ መዛሙርቱንም እንዲህ ይላቸው ጀመረ፥ “አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ፤ ይኸውም ግብዝነት ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 በዚያን ጊዜ የሕዝብ አእላፍ እርስ በርሳቸው እስኪረጋገጡ ድረስ ተሰብስበው ሳሉ፥ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር፦ አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ፥ እርሱም ግብዝነት ነው። ምዕራፉን ተመልከት |