Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 6:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ኢያሱም ለሕዝቡ ከተናገረ በኋላ፣ ሰባቱ ካህናት በእግዚአብሔር ፊት ሰባት ቀንደ መለከት ይዘው መለከታቸውን እየነፉ ወደ ፊት ቀደሙ፤ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦትም ተከተላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ኢያሱም ለሕዝቡ በተናገረ ጊዜ፥ ሰባቱ ካህናት ሰባቱን ቀንደ መለከት ይዘው በጌታ ፊት ሄዱ ቀንደ መለከቱንም ነፉ፤ የጌታ ቃል ኪዳን ታቦት ይከተላቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ኢያሱ ሕዝቡን ባዘዘው መሠረት በእግዚአብሔር ፊት ሰባት ቀንደ መለከት የያዙ ሰባት ካህናት ቀንደ መለከቱን እየነፉ ወደፊት ሄዱ፤ የእግዚአብሔርም የቃል ኪዳኑ ታቦት ተከተላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ይሄዱ ዘንድ ኢያሱ እንደ ነገ​ራ​ቸው ሰባቱ ካህ​ናት የተ​ቀ​ደሱ ሰባ​ቱን ቀንደ መለ​ከት ይዘው ሄዱ፤ በሄ​ዱም ጊዜ አሰ​ም​ተው በም​ል​ክት ነፉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሕጉ ታቦት ትከ​ተ​ላ​ቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ኢያሱም ለሕዝቡ በተናገረ ጊዜ፥ ሰባቱ ካህናት ሰባቱን ቀንደ መለከት ይዘው በእግዚአብሔር ፊት ሄዱ ቀንደ መለከቱንም ነፉ፥ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ይከተላቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 6:8
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚያም ሙሴ እንዲህ አላቸው፤ “ይህን ብታደርጉ ማለትም በእግዚአብሔር ፊት ታጥቃችሁ ለጦርነት ብትዘጋጁ፣


ሕዝቡንም፣ “ወደ ፊት ሂዱ፤ ከተማዋን ዙሩ፤ የታጠቁ ተዋጊዎችም በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ቀድመው ይሂዱ፤ ከተማዪቱንም ዙሩ” ሲል አዘዛቸው።


የታጠቁ ተዋጊዎችም መለከት ከሚነፉት ካህናት ፊት ቀድመው ሲሄዱ፣ ደጀን የሆኑት ጠባቂዎች ደግሞ ታቦቱን ተከተሉ፤ በዚህ ጊዜ ሁሉ መለከቶቹ ባለማቋረጥ ይነፉ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች