Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 30:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እኔን ሳይጠይቁ፣ ወደ ግብጽ ይወርዳሉ፤ የፈርዖንን ከለላ፣ የግብጽንም ጥላ ለመጠጊያነት ይፈልጋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ከአፌ ነገርን ሳይጠይቁ በፈርዖን ኃይል ለመጽናት በግብጽም ጥላ ለመታመን ወደ ግብጽ ይወርዳሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እኔን ሳያማክሩ ርዳታ ለመጠየቅ ወደ ግብጽ ይወርዳሉ፤ ግብጽ ከለላ እንድሆናቸው በመፈለግ በግብጽ ንጉሥ ይተማመናሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እኔን ሳይ​ጠ​ይቁ በፈ​ር​ዖን ኀይል ይረዱ ዘንድ በግ​ብ​ፅም ይጠ​በቁ ዘንድ ወደ ግብፅ ይሄ​ዳሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ከአፌ ነገርን ሳይጠይቁ በፈርዖን ኃይል ይጸኑ ዘንድ በግብጽም ጥላ ይታመኑ ዘንድ ወደ ግብጽ እንዲወርዱ ይሄዳሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 30:2
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢዮሣፍጥ ግን፣ “እንጠይቀው ዘንድ ሌላ የእግዚአብሔር ነቢይ እዚህ የለምን?” አለ።


የአሦር ንጉሥ ግን ሆሴዕ እንደ ከዳው ተገነዘበ፤ ምክንያቱም ወደ ግብጽ ንጉሥ ወደ ሲጎር መልክተኞች ስለ ላከና በየዓመቱም ያደርግ እንደ ነበረው ለአሦር ንጉሥ ስላልገበረ ነው፤ ከዚህም የተነሣ ስልምናሶር ይዞ ወህኒ ቤት አስገባው።


እነሆ፤ እንዲህ የምትመካባት ግብጽ የሚደገፍባትን ሰው እጅ ወግታ የምታቈስል፣ የተቀጠቀጠች ሸንበቆ ናት። የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንም ለሚመኩበት ሁሉ እንደዚሁ ነው።


“ምክር ለግሱን፤ ውሳኔ ስጡን፤ በቀትር ጥላችሁን እንደ ሌሊት አጥሉብን፤ የሸሹትን ደብቁ፤ ስደተኞችን አሳልፋችሁ አትስጡ።


በኢትዮጵያ ወንዞች ዳር ለምትገኝ፣ ፉር ፉር የሚሉ ክንፎች ላሉባት ምድር ወዮላት!


እነሆ፤ እንዲህ የምትመካባት ግብጽ የሚደገፍባትን ሰው እጅ ወግታ የምታቈስል የተቀጠቀጠች ሸንበቆ ናት! የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንም ለሚመኩበት ሁሉ እንደዚሁ ነው።


የምትመካው በግብጽ ሠረገሎችና ፈረሶች ሆኖ ሳለ ከጌታዬ የበታች የጦር ሹማምት እንኳ አንዱን እንዴት መመለስ ትችላለህ?


ሰዎች፣ የሚያነበንቡትንና የሚያንሾካሽኩትን ሟርተኞችንና መናፍስት ጠሪዎችን ጠይቁ ቢሏችሁ፣ ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ አይገባውምን? በሕያዋን ምትክ ሙታንን መጠየቅ ለምን አስፈለገ?


ከሺሖር ወንዝ ውሃ ለመጠጣት፣ አሁንስ ለምን ወደ ግብጽ ወረድሽ? ከኤፍራጥስ ወንዝስ ውሃ ለመጠጣት፣ ወደ አሦር መውረድ ለምን አስፈለገሽ?


“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሊወጋን ስለ ሆነ፣ እባክህን ፈጥነህ፣ እግዚአብሔርን ጠይቅልን፤ ምናልባት ንጉሡ ከእኛ ይመለስ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ቀድሞው ታምራት ያደርግልን ይሆናል” ብለው ነበር።


የፈርዖንም ሰራዊት ከግብጽ ወጥቶ ነበርና ኢየሩሳሌምን ከብበው የነበሩት ባቢሎናውያን ይህን ሲሰሙ ኢየሩሳሌምን ለቅቀው ሄዱ።


ደግሞም፣ ‘ጦርነት ወደማናይበት፣ የመለከት ድምፅ ወደማንሰማበትና ወደማንራብበት ወደ ግብጽ ምድር ሄደን በዚያ እንኖራለን’ ብትሉ፣


ነቢዩ ኤርምያስን እንዲህ አሉት፤ “ቀድሞ ብዙዎች ነበርን አሁን እንደምታየን ግን የቀረነው ጥቂት ነን፤ ስለዚህ እባክህ ልመናችንን ስማ፤ ለዚህ ለተረፈው ሕዝብ ሁሉ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ።


‘ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን፤ እርሱ ያለህን ሁሉ ንገረን፤ እኛም እንታዘዛለን’ ብላችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር በላካችሁኝ ጊዜ ሕይወታችሁን የሚያጠፋ ስሕተት ፈጸማችሁ።


የእግዚአብሔርንም ቃል ባለመታዘዝ ወደ ግብጽ ገቡ፤ ዘልቀውም እስከ ጣፍናስ ድረስ ሄዱ።


በእግዚአብሔር የተቀባው፣ የሕይወታችን እስትንፋስ፣ በወጥመዳቸው ተያዘ፤ በጥላው ሥር፣ በአሕዛብ መካከል እንኖራለን ብለን አስበን ነበር።


ወዮ ለእነርሱ፤ ከእኔ ርቀው ሄደዋልና! ጥፋት ይምጣባቸው! በእኔ ላይ ዐምፀዋልና። ልታደጋቸው ፈለግሁ፤ እነርሱ ግን በእኔ ላይ ሐሰት ይናገራሉ።


በአሕዛብ መካከል ራሳቸውን ቢሸጡም፣ እኔ አሁን እሰበስባቸዋለሁ፤ በንጉሥና በአለቆች ጭቈና ሥር፣ እየመነመኑ ይሄዳሉ።


ለብቻው እንደሚባዝን የዱር አህያ፣ ወደ አሦር ሄደዋልና፤ ኤፍሬም በእጅ መንሻ ወዳጅ አበጀ።


እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ሆኖ በኡሪም በመጠየቅ ውሳኔ በሚያስገኝለት በካህኑ በአልዓዛር ፊት ይቆማል፤ እርሱም ሆነ መላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ በአልዓዛር ትእዛዝ ይወጣሉ፤ በርሱም ቃል ይገባሉ።”


ዳግመኛ አትመለስባትም ባልሁህ መንገድም እግዚአብሔር በመርከብ ወደ ግብጽ ይመልስሃል። እዚያም ወንዶችና ሴቶች ባሮች እንድትሆኗቸው ለጠላቶቻችሁ ለመሸጥ ራሳችሁን ታቀርባላችሁ፤ የሚገዛችሁ ግን አይኖርም።


የእስራኤልም ሰዎች ከስንቃቸው ላይ ጥቂት ወሰዱ፤ ስለ ጕዳዩ ግን እግዚአብሔርን አልጠየቁም ነበር።


“የእሾኽ ቍጥቋጦውም ዛፎቹን፣ ‘በርግጥ ቀብታችሁ በላያችሁ የምታነግሡኝ ከሆነ መጥታችሁ በጥላዬ ሥር ተጠለሉ፤ ይህን ባታደርጉ ግን እሳት ከእሾኽ ቍጥቋጦው ይነሣ፤ የሊባኖስንም ዝግባዎች ይብላ!’ አላቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች