Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 21:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ጠባቂውም መለሰ፤ “ይነጋል፤ ግን ተመልሶ ይመሻል፤ መጠየቅ ከፈለጋችሁ፣ ጠይቁ፤ ነገር ግን ተመልሳችሁ ኑ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ጉበኛውም፦ “ይነጋል ደግሞም ይመሻል፤ ትጠይቁ ዘንድ ብትወድዱ ጠይቁ፤ ተመልሳችሁም ኑ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ዘብ ጠባቂውም “በእርግጥ የሌሊቱ ንጋት እየተቃረበ ነው፤ ነገር ግን ሌሊቱ ተመልሶ ይመጣል፤ እንደገና ጠይቀህ ለመረዳት ብትፈልግ ተመልሰህ ናና ጠይቅ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ጕበ​ኛ​ውም፥ “ይነ​ጋል፤ ደግ​ሞም ይመ​ሻል፤ ትጠ​ይቁ ዘንድ ብት​ወ​ድዱ ጠይቁ፤ ተመ​ል​ሳ​ች​ሁም ኑ፥” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ጕበኛውም፦ ይነጋል ደግሞም ይመሻል፥ ትጠይቁ ዘንድ ብትወድዱ ጠይቁ፥ ተመልሳችሁም ኑ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 21:12
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ፤ ሲመሽ ድንገተኛ ሽብር ሆነ! ከመንጋቱ በፊት ግን አንዳቸውም አልተገኙም። የዘረፉን ዕድል ፈንታ፣ የበዘበዙን ዕጣ ይህ ሆነ።


ስለ ዱማ የተነገረ ንግር፤ አንዱ ከሴይር ጠርቶኝ፣ “ጠባቂ ሆይ፤ ሊነጋ ምን ያህል ቀረው? ጠባቂ ሆይ፤ ሊነጋ ምን ያህል ቀረው?” አለኝ።


ስለ ዐረብ አገር የተነገረ ንግር፤ እናንተ በዐረብ ዱር የምትሰፍሩ፣ የድዳን ሲራራ ነጋዴዎች፣


ክፉ ሰው መንገዱን፣ በደለኛም ሐሳቡን ይተው። ወደ እግዚአብሔር ይመለስ፤ እርሱም ምሕረት ያደርግለታል፤ ወደ አምላካችን ይመለስ፤ ይቅርታው ብዙ ነውና።


ወይፈኖቿን ሁሉ ዕረዱ፤ ወደ መታረጃም ይውረዱ! የሚቀጡበት ጊዜ፣ ቀናቸው ደርሷልና ወዮላቸው!


እንዲህ በላቸው፤ ‘በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዳቸው ተመልሰው በሕይወት እንዲኖሩ እንጂ በክፉዎች ሞት ደስ አልሰኝም። ተመለሱ! ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ! የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ለምን ትሞታላችሁ?’


“ ‘እነሆ ቀኑ ይኸው ደረሰ! የጥፋት ፍርድ ተገልጧል፤ በትሩ አቈጥቍጧል፤ ትዕቢት አብቧል።


ጊዜው ደርሷል፤ ቀኑም ይኸው! መዓት በሕዝቡ ሁሉ ላይ ስለ መጣ፣ የሚገዛ አይደሰት፤ የሚሸጥም አይዘን።


ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶም እንዲህ ይላል፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ መልእክት ሰምተናል፤ መልእክተኛው ወደ አሕዛብ ተልኮ እንዲህ ብሏል፤ “ተነሡ፤ እርሷን ለመውጋት እንውጣ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች