Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 11:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የኤፍሬም ምቀኛነት ያከትማል፤ የይሁዳ ጠላቶችም ይቈረጣሉ፤ ኤፍሬም በይሁዳ አይቀናም፤ ይሁዳም ኤፍሬምን አይጠላም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የኤፍሬም ምቀኝነት ያከትማል፤ የይሁዳ ጠላቶችም ይቈረጣሉ፤ ኤፍሬም በይሁዳ አይቀናም፤ ይሁዳም ኤፍሬምን አይጠላም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከዚያን በኋላ የእስራኤል መንግሥት በይሁዳ ላይ ያለውን ምቀኝነት ይተዋል፤ ይሁዳም በእስራኤል ላይ ያለውን ጠላትነትና ጥላቻ ያቆማል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የኤ​ፍ​ሬ​ምም ቅናት ይሻ​ራል፤ የይ​ሁ​ዳም ጠላ​ቶች ይጠ​ፋሉ፤ ኤፍ​ሬ​ምም በይ​ሁዳ አይ​ቀ​ናም፤ ይሁ​ዳም ኤፍ​ሬ​ምን አያ​ስ​ጨ​ን​ቅም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የኤፍሬምም ምቀኝነት ይርቃል፥ ይሁዳንም የሚያስጨንቁ ይጠፋሉ፤ ኤፍሬምም በይሁዳ አይቀናም፥ ይሁዳም ኤፍሬምን አያስጨንቅም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 11:13
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምናሴ ኤፍሬምን፣ ኤፍሬም ምናሴን ይበላል፤ በይሁዳም ላይ በአንድነት ይነሣሉ። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።


በዚያ ዘመን የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት በአንድነት ሆነው ከሰሜን ምድር ለአባቶቻቸው ርስት አድርጌ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ይመጣሉ።


“ይህ ሕዝብ፣ ‘እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሁለቱን መንግሥታት ጥሏል’ እንደሚሉ አላስተዋልህምን? ሕዝቤን ንቀዋል፤ እንደ ሕዝብም አልቈጠሯቸውም።


“በዚያ ዘመን፣ በዚያ ጊዜም፤” ይላል እግዚአብሔር፤ “የእስራኤል ሕዝብና የይሁዳ ሕዝብ በአንድነት ይመጣሉ፤ አምላካቸውንም እግዚአብሔርን በመፈለግ እያለቀሱ ይመጣሉ።


“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የእስራኤልን ሕዝብ ከተበተኑባቸው አገሮች መካከል በምሰበስብበት ጊዜ፣ አሕዛብ እያዩ ቅድስናዬን በመካከላቸው እገልጣለሁ፤ ከዚያም በገዛ ምድራቸው ይኖራሉ፤ ይህም ለባሪያዬ ለያዕቆብ የሰጠሁት ነው።


የይሁዳ ሕዝብና የእስራኤል ሕዝብ እንደ ገና አንድ ይሆናሉ፤ አንድ መሪም ይሾማሉ፤ አንድ ሆነውም በምድሪቱ ይገንናሉ፤ የኢይዝራኤል ቀን ታላቅ ይሆናልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች