Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሆሴዕ 4:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እናንተ የእስራኤል ልጆች፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እግዚአብሔር በምድሪቱ በምትኖሩት ላይ የሚያቀርበው ክስ አለውና፤ ምክንያቱም ታማኝነት የለም፤ ፍቅርም የለም፤ እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድሪቱ የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ! እውነትና ጽኑ ፍቅር አምላክንም ማወቅ በምድሪቱ ስለ ሌለ ጌታ በምድሪቱ ላይ ከሚኖሩ ጋር ሙግት አለውና የጌታን ቃል ስሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በዚህች ምድር በሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ላይ እግዚአብሔር የሚያቀርበው ወቀሳ አለው፤ ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እርሱ የሚልህን ሁሉ ስማ፦ “በምድሪቱ ላይ ታማኝነትና ፍቅር እግዚአብሔርንም ማወቅ ጠፍቶአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ! እው​ነ​ትና ምሕ​ረት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ማወቅ በም​ድር ስለ​ሌለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ላይ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ይወ​ቅ​ሳ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እውነትና ምሕረት እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድር ስለሌለ እግዚአብሔር በምድሩ ላይ ከሚኖሩ ጋር ክርክር አለውና የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሆሴዕ 4:1
44 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚያም ሚክያስ እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ፣ የሰማይም ሰራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ።


በአንተ ዘንድ ባዕድ አምላክ አይኑር፤ ለሌላም አምላክ አትስገድ።


እናንተ የሰዶም ገዦች፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እናንተ የገሞራ ሰዎች፤ የአምላካችንን ሕግ አድምጡ።


“ኑና እንዋቀሥ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ኀጢአታችሁ እንደ ዐለላ ቢቀላ፣ እንደ በረዶ ይነጣል፤ እንደ ደም ቢቀላም፣ እንደ ባዘቶ ነጭ ይሆናል።


ስለዚህ በኢየሩሳሌም ያለውን ሕዝብ የምትገዙ፣ እናንተ ፌዘኞች የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።


እናንተ አሕዛብ ሆይ፤ ኑ አድምጡም፤ እናንተ ሰዎች ሆይ፤ አስተውሉ። ምድርና በውስጧ ያለ ሁሉ፣ ዓለምና ከርሷ የሚበቅል ሁሉ ይስማ!


እግዚአብሔር የበቀል ቀን፣ ስለ ጽዮንም የሚሟገትበት ዓመት አለውና።


“እናንተ በኢየሩሳሌም የምትኖሩና የይሁዳ ሰዎች ሆይ፤ በእኔና በወይኔ ቦታ መካከል እስኪ ፍረዱ።


ፍትሕን የሚጠራ ማንም የለም፤ ጕዳዩን በቅንነት የሚያቀርብ የለም፤ በከንቱ ነገር ታመኑ፤ ሐሰትን ተናገሩ፤ ሁከትን ፀነሱ፤ ክፋትንም ወለዱ።


የሰላምን መንገድ አያውቁም፤ በጐዳናቸውም ፍትሕ የለም፤ መንገዳቸውን ጠማማ አድርገውታል፤ በዚያም የሚሄድ ሰላም አያገኝም።


እናንተ በቃሉ የምትንቀጠቀጡ፣ ይህን የእግዚአብሔር ቃል ስሙ፤ “እናንተ ወንድሞቻችሁ የጠሏችሁ፣ ስለ ስሜም አውጥተው የጣሏችሁ፣ ‘እስኪ እግዚአብሔር ይክበርና፣ የእናንተን ደስታ እንይ!’ አሏችሁ፤ ይሁን እንጂ ማፈራቸው አይቀርም።


የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣ “ታዘዙኝ” በማለት ደጋግሜ አስጠነቀቅኋቸው።


እንዲህም በል፤ ‘የይሁዳ ነገሥታትና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ለሰሚው ሁሉ ጆሮ የሚዘገንን ክፉ ነገር እነሆ በዚህ ስፍራ አመጣለሁ፤


የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ የእስራኤል ቤት ወገን ሁላችሁ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።


“ስለዚህ እንደ ገና ከእናንተ ጋራ እፋረዳለሁ፤ ከልጅ ልጆቻችሁም ጋራ እከራከራለሁ።” ይላል እግዚአብሔር።


እግዚአብሔር ከሕዝቦች ጋራ ይፋረዳልና፣ ታላቅ ጩኸት እስከ ምድር ዳርቻ ያስተጋባል፤ በሰው ሁሉ ላይ ፍርድን ያመጣል፤ ክፉዎችንም ለሰይፍ ይዳርጋል’ ” ይላል እግዚአብሔር።


“ ‘ነገር ግን፣ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር ስለ አንተ እንዲህ ይላል፤ በሰይፍ አትሞትም፤


“ሕዝቤ ቂሎች ናቸው፤ እኔን አያውቁኝም። ማስተዋል የጐደላቸው፣ መረዳትም የማይችሉ ልጆች ናቸው። ክፋትን ለማድረግ ጥበበኞች፣ መልካም መሥራት ግን የማያውቁ።”


ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፤ ሰማያትም በላይ ይጨልማሉ፤ ተናግሬአለሁ፤ ሐሳቤን አልለውጥም፤ ወስኛለሁ፤ ወደ ኋላም አልልም።”


እኔም በልቤ እንዲህ አልሁ፤ “እነዚህ ድኾች ናቸው፤ ሞኞች ናቸው፤ የእግዚአብሔርን መንገድ፣ የአምላካቸውን ሕግ አላወቁምና።


ምድራቸው በእስራኤል ቅዱስ ፊት፣ በበደል የተሞላች ብትሆንም፣ እስራኤልንና ይሁዳን አምላካቸው የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር አልጣላቸውም።


“ከትንሹ እስከ ትልቁ ሰው፣ ሁሉም ለጥቅም የሚስገበገቡ ናቸው፤ ነቢያቱም ካህናቱም ሳይቀሩ፣ ሁሉም ያጭበረብራሉ።


ስለዚህ እንዲህ በላቸው፤ ‘ይህ ሕዝብ አምላኩን እግዚአብሔርን ያልታዘዘ፣ ምክሩን ያልተቀበለ ወገን ነው፤ እውነት ጠፍቷል፤ ከአንደበታቸውም ሸሽቷል።


እናንተ ሴቶች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ጆሮቻችሁን ከአንደበቱ ለሚወጡት ቃላት ክፈቱ፤ ሴቶች ልጆቻችሁን ዋይታ፣ አንዳችሁም ሌላውን ሙሾ አስተምሩ።


“ሐሰትን ለመናገር፣ ምላሳቸውን እንደ ቀስት ገተሩ፤ በእውነት ሳይሆን፣ በሐሰት በምድሪቱ ገነኑ፤ ከክፋት ወደ ክፋት ሄዱ፤ እኔንም አላወቁኝም፤” ይላል እግዚአብሔር።


ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ እንደ ብረት አነጥራቸዋለሁ፤ እፈትናቸዋለሁም፤ ስለ ሕዝቤ ኀጢአት፣ ከዚህ የተለየ ምን ማድረግ እችላለሁ?


“ ‘አንቺ አመንዝራ ሆይ፤ እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስሚ!


እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ የሚያቀርበው ክስ አለው፤ ያዕቆብን እንደ መንገዱ ይቀጣዋል፤ እንደ ሥራውም ይከፍለዋል።


በማሕፀን ሳለ የወንድሙን ተረከዝ ያዘ፤ ሙሉ ሰውም ሲሆን ከአምላክ ጋራ ታገለ።


“እናንተ ካህናት፤ ይህን ስሙ! የእስራኤል ቤት፤ አስተውሉ! የንጉሥ ቤት ሆይ፤ አድምጡ! ይህ ፍርድ በእናንተ ላይ ነው፤ በምጽጳ ወጥመድ፣ በታቦርም ላይ የተዘረጋ መረብ ሆናችኋልና።


“የሠሩት ሥራ፣ ወደ አምላካቸው እንዲመለሱ አይፈቅድላቸውም፤ የአመንዝራነት መንፈስ በልባቸው አለ፤ እግዚአብሔርንም አያውቁትም።


እናንተ ሽማግሌዎች፣ ይህን ስሙ፤ በምድሪቱም የምትኖሩ ሁላችሁ፣ አድምጡ፤ በእናንተ ዘመንም ሆነ በአባቶቻችሁ ዘመን፣ እንዲህ ዐይነት ነገር ሆኖ ያውቃልን?


የእስራኤል ልጆች ሆይ፤ እግዚአብሔር በእናንተ ከግብጽ ባወጣሁት ሕዝብ ሁሉ ላይ የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፤


እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ። “አንተ፣ ‘በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፤ በይሥሐቅም ቤት ላይ አትስበክ’ ትላለህ።


“ተራሮች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ክስ አድምጡ፤ እናንተ የምድር ጽኑ መሠረቶችም፣ ስሙ፤ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋራ ክርክር አለውና፤ ከእስራኤልም ጋራ ይፋረዳል።


እናንተ ባታውቁትም እኔ ዐውቀዋለሁ፤ አላውቀውም ብል፣ እኔም እንደ እናንተው ሐሰተኛ እሆናለሁ። እኔ ግን ዐውቀዋለሁ፤ ቃሉንም እጠብቃለሁ።


ከዚህም በላይ በሐሳባቸው እግዚአብሔርን ማወቅ አይጠቅምም በማለታቸው፣ መደረግ የማይገባውን እንዲያደርጉ እግዚአብሔር ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው።


ወደ ሰከነ ልቡናችሁ ተመለሱ፤ ኀጢአትንም አትሥሩ፤ እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉና፤ ይህንም የምለው ላሳፍራችሁ ነው።


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ፤ ድል የሚነሣም በሁለተኛው ሞት ከቶ አይጐዳም።


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች