Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ገላትያ 5:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የምለውን አስተውሉ! ትገረዙ ዘንድ ብትፈልጉ፣ ክርስቶስ ፈጽሞ ለእናንተ እንደማይበጃችሁ እኔ ጳውሎስ እነግራችኋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እነሆ እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ፥ ብትገረዙ ክርስቶስ ምንም አይጠቅማችሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እነሆ! እኔ ጳውሎስ የምላችሁ ይህ ነው፤ “መገረዝ ያስፈልገናል” ብላችሁ ብትገረዙ ክርስቶስ ምንም አይጠቅማችሁም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እነሆ፥ እኔ ጳው​ሎስ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ “ብት​ገ​ዘ​ሩም በክ​ር​ስ​ቶስ ዘንድ ምንም አይ​ጠ​ቅ​ማ​ች​ሁም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እነሆ፥ እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ፦ ብትገረዙ ክርስቶስ ምንም አይጠቅማችሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ገላትያ 5:2
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንዳንድ ሰዎችም ከይሁዳ ወደ አንጾኪያ ወርደው፣ “በሙሴ ሥርዐት መሠረት ካልተገረዛችሁ ልትድኑ አትችሉም” በማለት ወንድሞችን ማስተማር ጀመሩ።


አንዳንድ ሰዎች ያለ እኛ ፈቃድ ከእኛ ዘንድ ወጥተው በንግግራቸው ልባችሁን እንዳወኩና እንዳናወጧችሁ ሰምተናል።


ከፈሪሳውያን ወገን ያመኑት አንዳንዶቹ ተነሥተው በመቆም፣ “አሕዛብ እንዲገረዙና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ማድረግ አስፈላጊ ነው” አሉ።


ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ የጻፍሁት እኔ ጳውሎስ ነኝ።


እኔ ጳውሎስ፣ በእናንተ ፊት ስሆን “ዐይነ ዐፋር”፣ ከእናንተ ስርቅ ግን፣ “ደፋር” የተባልሁ በክርስቶስ የዋህነትና ገርነት እለምናችኋለሁ።


ወንድሞች ሆይ፤ እስከ ዛሬ ስለ መገረዝ የምሰብክ ከሆነ፣ ታዲያ እስከ አሁን ለምን ያሳድዱኛል? እንደዚያማ ቢሆን ኖሮ፣ መስቀል ዕንቅፋት መሆኑ በቀረ ነበር።


በክርስቶስ ኢየሱስ ከሆኑ፣ መገረዝ ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና፤ የሚጠቅመውስ በፍቅር የሚገለጽ እምነት ብቻ ነው።


ወደ እናንተ ለመምጣት ፈልገን ነበር፤ በተለይም እኔ ጳውሎስ ብዙ ጊዜ ሞክሬ ነበር፤ ነገር ግን ሰይጣን አዘገየን።


እኔ ጳውሎስ ይህን በገዛ እጄ ጽፌልሃለሁ፤ ያለበትን እኔው እከፍልሃለሁ። አንተም ራስህ የእኔ ስለ መሆንህ ምንም አልናገርም።


በፍቅር እለምንሃለሁ፤ እንግዲህ ሽማግሌና አሁን ደግሞ የክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ የሆንሁት እኔ ጳውሎስ፣


ለእነዚያ እንደ ተሰበከ ለእኛም ደግሞ ወንጌል ተሰብኮልናልና። ነገር ግን ሰሚዎቹ ቃሉን ከእምነት ጋራ ስላላዋሐዱት አልጠቀማቸውም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች