Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዳንኤል 2:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 “ንጉሥ ሆይ፤ ተኝተህ ሳለ፣ አእምሮህ ወደ ፊት ሊሆን ስላለው ነገር ያሰላስል ነበር፤ ምስጢርን ገላጭ የሆነውም ወደ ፊት የሚሆነውን ነገር አሳየህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 “ንጉሥ ሆይ! አንተ በአልጋህ ላይ ተኝተህ ሳለ ወደ ፊት ስለሚሆነው ነገር ታሰላስል ነበር፤ ስለዚህ ምሥጢርን የሚገልጥ አምላክ ወደፊት የሚሆነውን ነገር አስታወቀህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 አንተ፥ ንጉሥ ሆይ፥ ከአንተ በኋላ የሚሆነው ምን እንደ ሆነ በአልጋህ ላይ ታስብ ነበር፥ ምሥጢርንም የሚገልጠው የሚሆነውን ነገር አስታውቆሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዳንኤል 2:29
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ አለው፤ “ሁለቱም የፈርዖን ሕልሞች ተመሳሳይና አንድ ዐይነት ናቸው፤ እግዚአብሔር ወደ ፊት የሚያደርገውን ለፈርዖን ገልጦለታል።


“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በዚያ ቀን ሐሳብ ወደ አእምሮህ ይመጣል፤ ክፋትንም ታውጠነጥናለህ።


የጠለቀውንና የተሰወረውን ነገር ይገልጣል፤ በጨለማ ያለውን ያውቃል፤ ብርሃንም ከርሱ ጋራ ይኖራል።


የአባቶቼ አምላክ ሆይ፤ አመሰግንሃለሁ፤ አከብርሃለሁም፤ ጥበብንና ኀይልን ሰጥተኸኛልና፤ ከአንተ የጠየቅነውን ነገር አሳውቀኸኛል፤ የንጉሡን ሕልም አሳውቀኸናል።”


ነገር ግን ምስጢርን የሚገልጥ አምላክ በሰማይ አለ፤ እርሱም በሚመጡት ዘመናት የሚሆነውን ነገር ለንጉሥ ናቡከደነፆር ገልጧል፤ በዐልጋህ ላይ ተኝተህ ሳለ በአእምሮህ የነበረው ሕልምና ራእይ ይህ ነው፤


የሰው እጅ ሳይነካው ከተራራ ተፈንቅሎ የወረደውና ብረቱን፣ ናሱን፣ ሸክላውን፣ ብሩንና ወርቁን ያደቀቀው ድንጋይ ራእይ ትርጓሜ ይህ ነው፤ “ታላቁ አምላክ ወደ ፊት የሚሆነውን ለንጉሡ አሳይቶታል፤ ሕልሙ እውነት ነው፤ ትርጓሜውም የታመነ ነው።”


ንጉሡም ዳንኤልን፣ “ይህን ምስጢር ልትገልጥ ችለሃልና፣ በእውነት አምላካችሁ የአማልክት አምላክና የነገሥታት ጌታ፣ ምስጢርንም ገላጭ ነው” አለው።


ተራሮችን የሚሠራ፣ ነፋስን የሚፈጥር፣ ሐሳቡንም ለሰው የሚገልጥ፣ ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፣ የምድርንም ከፍታዎች የሚረግጥ፣ ስሙ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች