ዳንኤል 2:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ኮከብ ቈጣሪዎቹም ለንጉሡ እንዲህ ብለው መለሱ፤ “ንጉሡ የጠየቀውን ጥያቄ ሊመልስ የሚችል ሰው በምድር ላይ አይገኝም! ማንም ንጉሥ ምንም ያህል ታላቅና ኀያል ቢሆን፣ እንዲህ ዐይነት ነገር ማንኛውንም ጠንቋይ፣ አስማተኛ ወይም ኮከብ ቈጣሪን ጠይቆ አያውቅም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 የከለዳውያን ኮከብ ቈጣሪዎቹም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦ “ንጉሥ ሆይ! አንተ ለማወቅ የምትፈልገውን ነገር ሊነግርህ የሚችል ሰው በዓለም ላይ አይገኝም፤ አንድ ንጉሥ የቱንም ያኽል ታላቅና ብርቱ ቢሆን ይህን የመሰለ ጥያቄ ለጠንቋዮች፥ ለአስማተኞችና ለኮከብ ቈጣሪዎች አቅርቦ አያውቅም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ከለዳውያኑም በንጉሡ ፊት መልሰው፦ የንጉሡን ነገር ያሳይ ዘንድ የሚችል ሰው በምድር ላይ የለም፥ ከነገሥታትም ታላቅና ኃይለኛ የሆነ እንደዚህ ያለ ነገር የሕልም ተርጓሚንና አስማተኛን ከለዳዊውንም አልጠየቀም። ምዕራፉን ተመልከት |