Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 20:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከዚያም ንጉሡ አሜሳይን፣ “የይሁዳ ሰዎች ሁሉ በሦስት ቀን ውስጥ፣ ወደ እኔ እንዲመጡ ጥራልኝ፤ አንተ ራስህም ተገኝ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከዚያም ንጉሡ አማሳይን፥ “የይሁዳ ሰዎች ሁሉ በሦስት ቀን ውስጥ፥ ወደ እኔ እንዲመጡ ጥራልኝ፤ አንተ ራስህም እንድትገኝ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ንጉሡም ዐማሣን “የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ጠርተህ በአንድነት ሰብስብና ከነገ ወዲያ ይዘሃቸው ወደዚህ ተመለስ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ንጉ​ሡም አሜ​ሳ​ይን፥ “የይ​ሁ​ዳን ሰዎች ሁሉ በሦ​ስት ቀን ውስጥ ጥራ​ልኝ፤ አን​ተም አብ​ረህ በዚህ ሁን” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ንጉሡም አሜሳይን፦ የይሁዳን ሰዎች ሁሉ በሦስት ቀን ውስጥ ጥራልኝ፥ አንተም አብረህ በዚህ ሁን አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 20:4
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤሴሎምም በኢዮአብ ምትክ አሜሳይን በሰራዊቱ ላይ ሾመ፤ አሜሳይ የእስማኤላዊው የዮቴር ልጅ ነበረ፤ ዮቴርም የኢዮአብን እናት፣ የጽሩያን እኅት፣ የናዖስን ልጅ አቢግያን አግብቶ ነበር።


አሜሳይንም፣ ‘አንተስ የዐጥንቴ ፍላጭ፣ የሥጋዬ ቍራጭ አይደለህምን? ከአሁን ጀምሮ እስከ ሕይወትህ ፍጻሜ በኢዮአብ ምትክ የሰራዊቴ አዛዥ ባላደርግህ፣ እግዚአብሔር ክፉ ያድርግብኝ፣ ከዚህ የባሰም ያምጣብኝ’ ብላችሁ ንገሩት።”


እርሱም የይሁዳን ሰዎች ልብ ሁሉ እንደ አንድ ሰው ልብ አድርጎ ማረከው፤ እነርሱም “አንተም ሰዎችህም ሁሉ ተመለሱ” ብለው ወደ ንጉሡ ላኩበት።


አቢግያ አሜሳይን ወለደች፤ አባቱም ዬቴር የተባለ እስማኤላዊ ነበረ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች