Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 10:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ዳዊትም፣ “አባቱ ቸርነትን እንዳደረገልኝ ሁሉ፣ እኔም ለናዖስ ልጅ ለሐኖን ወሮታውን ልክፈል” ሲል ዐሰበ። ስለዚህ ስለ አባቱ ሞት የተሰማውን ሐዘን እንዲገልጹለት ዳዊት መልክተኞችን ላከ። የዳዊት ሰዎች ወደ አሞናውያን ምድር በደረሱ ጊዜ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ዳዊትም፥ “አባቱ ቸርነትን እንዳደረገልኝ ሁሉ፥ እኔም ለናዖስ ልጅ ለሐኑን ቸርነት አደርጋለሁ” አለ። ስለዚህ ስለ አባቱ ሞት የተሰማውን ኀዘን እንዲገልጹለት ዳዊት መልክተኞችን ላከ። የዳዊት ሰዎች ወደ አሞናውያን ምድር በደረሱ ጊዜ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ንጉሥ ዳዊትም “አባቱ ናዖስ ለእኔ እንዳደረገልኝ ሁሉ እኔም ለልጁ ለሐኑን ታማኝ ወዳጅ በመሆን ወሮታውን እከፍላለሁ” አለ። ስለዚህም ዳዊት የሐዘን ተካፋይነቱን ለመግለጥ መልእክተኞች ላከ። መልእክተኞቹም ዐሞን በደረሱ ጊዜ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ዳዊ​ትም፥ “አባቱ ቸር​ነ​ትን እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ልኝ እኔ ለና​ዖስ ልጅ ለሐ​ኖን ቸር​ነት አደ​ር​ጋ​ለሁ” አለ። ዳዊ​ትም ስለ አባቱ ያጽ​ና​ኑት ዘንድ ብላ​ቴ​ኖ​ቹን ላከ፤ የዳ​ዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖች ወደ አሞን ልጆች ሀገር መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ዳዊትም፦ አባቱ ወረታ እንዳደረገልኝ እኔ ለናዖስ ልጅ ለሐኖን ቸርነት አደርጋለሁ አለ። ዳዊትም አባቱ ስለ ሞተ ሊያጽናናው ባሪያዎቹን ላከ፥ የዳዊትም ባሪያዎች ወደ አሞን ልጆች አገር መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 10:2
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊት መሃናይም ሲደርስ፣ ከአሞናውያን ከተማ ከረባት የመጣው፣ የናዖስ ልጅ ሾቢ፣ ከሎደባር የመጣው የዓሚኤል ልጅ ማኪርና ከሮግሊም የመጣው ገለዓዳዊው ቤርዜሊ


አሞናዊው ናዖስ ወጥቶ ኢያቢስ ገለዓድን ከበባት፤ የኢያቢስም ሰዎች ሁሉ፣ “ከእኛ ጋራ ቃል ኪዳን አድርግ፣ እኛም እንገዛልሃለን” አሉት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች