Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 1:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 “እናንተ የእስራኤል ቈነጃጅት ሆይ፤ ሐምራዊ ቀሚስና ቀጭን ፈትል ላለበሳችሁ፣ ልብሶቻችሁንም በወርቀ ዘቦ ላስጌጠላችሁ፣ ለሳኦል አልቅሱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 እናንት የእስራኤል ቆነጃጅት ሆይ! ሐምራዊ ቀሚስና ቀጭን ፈትል ላለበሳችሁ፥ ልብሶቻችሁንም በወርቀ ዘቦ ላስጌጠላችሁ፥ ለሳኦል አልቅሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 “የእስራኤል ሴቶች ሆይ! ውድ የሆነ ሐምራዊ ቀሚስ ያለብሳችሁ ለነበረው በወርቀ ዘቦም ላስጌጣችሁ፥ ለሳኦል አልቅሱለት!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የእ​ስ​ራ​ኤል ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ቀይ ሐርና ጥሩ ግምጃ ያለ​ብ​ሳ​ችሁ ለነ​በረ፥ በወ​ር​ቀ​ዘ​ቦም ያስ​ጌ​ጣ​ችሁ ለነ​በረ ለሳ​ኦል አል​ቅ​ሱ​ለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 የእስራኤል ቈነጃጅት ሆይ፥ ቀይ ሐርና ጥሩ ግምጃ ያለብሳችሁ ለነበረ፥ በወርቀዘቦም ላስጌጣችሁ ለሳኦል አልቅሱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 1:24
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሳኦልና ዮናታን በሕይወት እያሉ፣ የሚዋደዱና የሚስማሙ ነበሩ፤ ሲሞቱም አልተለያዩም፤ ከንስርም ይልቅ ፈጣኖች፣ ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ።


“ኀያላን እንዴት እንዲህ በጦርነት ወደቁ! ዮናታን በኰረብቶችህ ላይ ተወግቶ ሞቷል።


“የሰራዊት ነገሥታት ፈጥነው ይሸሻሉ፤ በሰፈር የዋሉ ሴቶችም ምርኮን ተካፈሉ።


የጠቢብ ሰው ዘለፋ ለሚሰማ ጆሮ፣ እንደ ወርቅ ጕትቻ ወይም እንደ ጥሩ የወርቅ ጌጥ ነው።


በረዶ ቢጥል ለቤተ ሰዎቿ አትሠጋም፤ ሁሉም ቀይ ልብስ ለብሰዋልና።


ለመሆኑ ቈንጆ ጌጣጌጧን፣ ሙሽራ የሰርግ ልብሷን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን፣ እጅግ ብዙ ቀን ረስቶኛል።


‘ምርኮ አግኝተው እየተከፋፈሉ፣ እያንዳንዱም ሰው አንዲት ወይም ሁለት ልጃገረዶች እየወሰደ አይደለምን? ይህ ሁሉ ምርኮ፣ በቀለም ያጌጡ ልብሶች ለሲሣራ ደርሰውት፣ በጌጣጌጥ የተጠለፉ ልብሶች ለዐንገቴ ይዞልኝ እየመጣ አይደለምን?’


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች