Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 1:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ለሳኦልና ለልጁ ለዮናታን፣ ለእግዚአብሔር ሰራዊትና ለእስራኤል ቤት ዐዘኑ፤ አለቀሱ፤ እስከ ማታም ድረስ ጾሙ፤ የወደቁት በሰይፍ ነበርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የወደቁት በሰይፍ ነበርና፥ ለሳኦልና ለልጁ ለዮናታን፥ ለጌታ ሠራዊትና ለእስራኤል ቤትም አዘኑ፤ አለቀሱ፤ እስከ ማታም ድረስ ጾሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በሰይፍ ስለ ተገደሉ ለሳኦል፥ ለልጁ ለዮናታንና ለእግዚአብሔር ሠራዊት ለመላው እስራኤል እስከ ምሽት ድረስ በመጾም በከባድ ሐዘን አለቀሱላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በጦር ወድ​ቀ​ዋ​ልና ለሳ​ኦ​ልና ለልጁ ለዮ​ና​ታን፥ ለይ​ሁ​ዳም ሕዝብ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ወገን እንባ እያ​ፈ​ሰሱ አለ​ቀሱ፤ እስከ ማታም ድረስ ጾሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በሰይፍም ወድቀዋልና ለሳኦልና ለልጁ ለዮናታን ለእግዚአብሔርም ሕዝብ ለእስራኤልም ወገን እንባ እያፈሰሱ አለቀሱ፥ እስከ ማታም ድረስ ጾሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 1:12
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እህል በሚቀምስበት ሰዓት ወደ ዳዊት መጥተው ምግብ እንዲበላ አጥብቀው ለመኑት። ዳዊት ግን፣ “ፀሓይ ከመጥለቋ በፊት እንጀራ ወይም ሌላ ነገር ብቀምስ፣ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ ከዚህም የባሰ ያምጣብኝ” ብሎ ማለ።


ጠላትህ ሲወድቅ ደስ አይበልህ፤ ሲሰናከልም ልብህ ሐሤት አያድርግ፤


ስለ ታረዱት ወገኖቼ፣ ቀንና ሌሊት አለቅስ ዘንድ፣ ምነው፣ ራሴ የውሃ ምንጭ በሆነ! ምነው ዐይኖቼ የእንባ መጕረፊያ በሆኑልኝ!


በፋጋ የወይን ጠጅ ለምትጠጡ፣ ምርጥ ሽቱም ለምትቀቡ፣ ስለ ዮሴፍ መከራ ግን ለማታዝኑ ወዮላችሁ!


እኔ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ ለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ እላችኋለሁ፤


ደካማ ማን ነው? እኔስ አብሬ አልደክምምን? በኀጢአት የሚሰናከል ማን ነው? እኔስ አልቈጭምን?


በመጨረሻም ሁላችሁ በአንድ ሐሳብ ተስማሙ፤ እርስ በርሳችሁ ተሳሰቡ፤ እንደ ወንድማማቾች ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ።


ከዚያም ዐጥንቶቻቸውን ወስደው በኢያቢስ ባለው የአጣጥ ዛፍ ሥር ቀበሩ፤ ሰባት ቀንም ጾሙ።


ሳኦልና ሦስት ልጆቹ፣ ዐብረውት የነበሩ ሰዎች ሁሉና ጋሻ ጃግሬው የሞቱት በአንድ ላይ በዚያ ቀን ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች