Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ዜና መዋዕል 30:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 መልእክተኞችም በንጉሡ ትእዛዝ፣ የንጉሡንና የሹማምቱን ደብዳቤ ይዘው ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ሄዱ፤ ደብዳቤውም እንዲህ የሚል ነበር፤ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፤ እርሱ ወደ ተረፋችሁት፣ ከአሦር ነገሥታትም እጅ ወዳመለጣችሁት፣ ወደ እናንተ እንዲመለስ እናንተም የአብርሃም፣ የይሥሐቅና የእስራኤል አምላክ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እንደ ንጉሡም ትእዛዝ መልክተኞቹ እንዲህ የሚለውን የንጉሡንና የሹማምንቱን ደብዳቤ ይዘው ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ሄዱ እንዲህም አሉ፦ “የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታ ከአሦር ነገሥታት እጅ ወዳመለጠ የእናንተ ወደ ሆኑት ትሩፋን እንዲመለስ ወደ አብርሃምና ወደ ይስሐቅ ወደ እስራኤልም አምላክ ተመለሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በንጉሡ ትእዛዝ መልእክተኞቹ እንዲህ የሚለውን የንጉሡንና የሕዝቡን ደብዳቤ ይዘው ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ሄዱ። “የእስራኤል ልጆች ሆይ! ከአሦር ንጉሥ ምርኮ የተረፋችሁት ወደ እናንተ ይመለስ ዘንድ፥ ወደ አብርሃም፥ ወደ ይስሐቅና ወደ ያዕቆብ አምላክ ተመለሱ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እንደ ንጉ​ሡም ትእ​ዛዝ መል​እ​ክ​ተ​ኞቹ እን​ዲህ የሚ​ለ​ውን የን​ጉ​ሡ​ንና የአ​ለ​ቆ​ቹን ደብ​ዳቤ ይዘው ወደ እስ​ራ​ኤ​ልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ፈጥ​ነው ሄዱ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ሦር ንጉሥ እጅ ወዳ​መ​ለጠ ቅሬ​ታ​ችሁ እን​ዲ​መ​ለስ ወደ አብ​ር​ሃ​ምና ወደ ይስ​ሐቅ ወደ ያዕ​ቆ​ብም አም​ላክ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ለሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እንደ ንጉሡም ትእዛዝ መልክተኞቹ እንዲህ የሚለውን የንጉሡንና የአለቆቹን ደብዳቤ ይዘው ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ሄዱ፤ “የእስራኤል ልጆች ሆይ! እግዚአብሔር ከአሦር ነገሥታት እጅ ወዳመለጠ ቅሬታችሁ እንዲመለስ ወደ አብርሃምና ወደ ይስሐቅ ወደ እስራኤልም አምላክ ተመለሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ዜና መዋዕል 30:6
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሠርክ መሥዋዕት በሚቀርብበትም ጊዜ፣ ኤልያስ ወደ መሠዊያው ቀረብ ብሎ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “የአብርሃም፣ የይሥሐቅና የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ የእስራኤል አምላክ መሆንህ፣ እኔም የአንተ አገልጋይ መሆኔና ይህን ሁሉ በትእዛዝህ እንዳደረግሁ ዛሬ ይታወቅ።


ከዚያም የአሦር ንጉሥ ፎሓ ምድሪቱን ወረረ፤ ምናሔም ርዳታውን ለማግኘትና በመንግሥቱ ላይ ያለውን ይዞታ ለማጽናት ሲል፣ አንድ ሺሕ መክሊት ብር ሰጠው።


በእስራኤል ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን፣ የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጥቶ ዒዮን፣ አቤልቤትመዓካን፣ ያኖዋን፣ ቃዴስንና አሦርን፣ ገለዓድንና ገሊላን፣ የንፍታሌምንም ምድር ጭምር ያዘ፤ ሕዝቡንም ማርኮ ወደ አሦር ወሰደው።


የአባቶቻችን የአብርሃም፣ የይሥሐቅ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን ሐሳብ ለዘላለም በሕዝብህ ልብ ጠብቀው፤ ልባቸውንም ለአንተ ታማኝ አድርገው።


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የአሦርን ንጉሥ የፎሓን መንፈስ ይኸውም የቴልጌልቴልፌልሶርን መንፈስ አነሣሥቶ የሮቤልን፣ የጋድንና፣ የምናሴን ነገድ እኩሌታ ማርኮ እንዲወስድ አደረገ። እነዚህንም ወደ አላሔ፣ ወደ አቦር፣ ወደ ሃራና ወደ ጎዛን ወንዝ ዳርቻ አፈለሳቸው፤ እነርሱም እስከ ዛሬ ድረስ በዚያ ይገኛሉ።


የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር ወደ እርሱ መጥቶ ነበር፤ ሆኖም ችግር ፈጠረበት እንጂ አልረዳውም።


አዳር በተባለው በዐሥራ ሁለተኛው ወር፣ በዐሥራ ሦስተኛው ቀን ወጣት፣ ሽማግሌ፣ ሴትና ሕፃን ሳይባል አይሁድ ሁሉ በዚያ ዕለት እንዲጠፉ፣ እንዲገደሉና እንዲደመሰሱ፣ ሀብታቸውም እንዲዘረፍ ደብዳቤ ለንጉሡ አውራጃዎች ሁሉ በመልእክተኞች እጅ ተላከ።


በቤተ መንግሥቱ ፈረሶች የተቀመጡ መልእክተኞችም፣ በንጉሡ አስቸኳይ ትእዛዝ ጋልበው ወጡ፤ ዐዋጁም በሱሳ ግንብ ተነገረ።


“ዘመኔ ከሚሮጥ ሰው ይልቅ ይፈጥናል፤ አንዳችም ደስታ ሳያይ ያልፋል።


የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘር ባያስቀርልን ኖሮ፣ እንደ ሰዶም በሆንን፣ ገሞራንም በመሰልን ነበር።


ከዐሥር አንድ ሰው እንኳ በምድሪቱ ቢቀር፣ እርሱም ደግሞ ይጠፋል፤ ነገር ግን የኮምበልና የወርካ ዛፍ በተቈረጠ ጊዜ ጕቶ እንደሚቀር፣ ቅዱሱም ዘር እንዲሁ በምድሪቱ ጕቶ ሆኖ ይቀራል።”


ነቢዩ ኤርምያስ በምርኮ ተወስደው በሕይወት ለቀሩት ሽማግሌዎች፣ ለካህናቱ፣ ለነቢያቱና ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማርኮ ለወሰዳቸው ሕዝብ ሁሉ የላከው የደብዳቤ ቃል ይህ ነው፤


“ከዳተኛ ልጆች ሆይ፤ እኔ ባለቤታችሁ ነኝና ተመለሱ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ከአንድ ከተማ አንድ፣ ከአንድ ነገድ ሁለት መርጫችሁ ወደ ጽዮን አመጣችኋለሁ።


“እስራኤል ሆይ፤ ብትመለስ፣ ወደ እኔ ብትመለስ” ይላል እግዚአብሔር፤ “አስጸያፊ ነገሮችህን ከፊቴ ብታስወግድ፣ ባትናወጥ ብትቆምም፣


ከተማዪቱ ሙሉ በሙሉ መያዟን፣ ለባቢሎን ንጉሥ ለመንገር፣ አንዱ ወሬኛ ሌላውን ወሬኛ፣ አንዱ መልእክተኛ ሌላውን መልእክተኛ ወዲያው ወዲያው ይከተላል፤


መንገዳችንን እንመርምር፤ እንፈትን፤ ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ መልሰን፤ እኛም እንመለሳለን፤ ዘመናችንን እንደ ቀድሞው አድስ፤


እንዲህ በላቸው፤ ‘በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዳቸው ተመልሰው በሕይወት እንዲኖሩ እንጂ በክፉዎች ሞት ደስ አልሰኝም። ተመለሱ! ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ! የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ለምን ትሞታላችሁ?’


እስራኤል ሆይ፤ በኀጢአትህ ምክንያት ስለ ወደቅህ፣ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ።


“ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰባብሮናል፤ እርሱም ይጠግነናል፤ እርሱ አቍስሎናል፤ እርሱም ይፈውሰናል።


ስለዚህ ለሕዝቡ ንገር፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ወደ እኔ ተመለሱ፤’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ‘እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፤’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


የቀደሙት ነቢያት፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ‘ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ’ ይላል በማለት ለአባቶቻችሁ ሰብከው ነበር፤ እነርሱ ግን አልሰሙም፤ እኔንም አላደመጡም፤ እንደ እነርሱ አትሁኑ፤” ይላል እግዚአብሔር።


ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፤ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል። እናንተ ኀጢአተኞች እጃችሁን አንጹ፤ እናንተ በሁለት ሐሳብ የምትዋልሉ ልባችሁን አጥሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች