Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 80:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ሐዘንን እንደ ምግብ፥ እንባንም እንደ መጠጥ በብዛት ሰጠሃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የእንባ እንጀራ አበላሃቸው፤ ስፍር የሞላ እንባም አጠጣሃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የሠራዊት አምላክ አቤቱ፥ በሕዝብህ ጸሎት ላይ እስከ መቼ ትቈጣለህ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ወደ ግብፅ ሀገር በሄደ ጊዜ ለዮ​ሴፍ ምስ​ክ​ርን አቆመ። የማ​ያ​ው​ቀ​ውን ቋንቋ ሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 80:5
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለዚህ ዐይነቱ ምግብ ፍላጎት የለኝም፤ ብበላውም እንኳ ጤና ይነሣኛል።


ምግቤ ዐመድ ሆኖአል፤ እንባዬም ከምጠጣው ነገር ጋር ተደባልቆአል፤


ቀንና ሌሊት ስለ ማልቅስ እንባዬ እንደ ምግብ ሆኖኛል፤ ጠላቶቼ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ ዘወትር ይጠይቁኛል።


አምላክ ሆይ! እንደዚህ ለምን ተውከን? ሕዝብህንስ የምትቈጣው ለዘለዓለም ነውን?


እግዚአብሔር ሆይ! በእኛ ላይ የምትቈጣው እስከ መቼ ድረስ ነው? ቅናትህ እንደ እሳት ሲነድ ይኖራልን?


በብዙ መከራ ውስጥ እንድታልፉ እግዚአብሔር ይፈቅድ ይሆናል፤ ነገር ግን እርሱ ራሱ ከእናንተ ጋር በመገኘት ያስተምራችኋል፤ ዳግመኛም እርሱን በመፈለግ አትደክሙም።


“በቊጣ ተሞልተህ አሳደድከን ያለ ርኅራኄ ገደልከን።


ጸሎት አልፎ ሊገባ በማይችልበት ራስህን ጥቅጥቅ ባለ ደመና ሸፈንክ። መኖሪያህን በደመና ሸፈንክ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች