Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 74:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ጠላቶችህ ዘወትር የሚጮኹትን ጩኸትና የሚደነፉትን ድንፋታ አስታውስ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 የባላጋራዎችህን ድንፋታ፣ ዘወትር የሚነሣውን የጠላቶችህን ፉከራ አትርሳ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 የጠላቶችህን ቃል አትርሳ፥ የተቃዋሚዎችህ ድንፋታ ሳያቋርጥ ወደ አንተ ይወጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 74:23
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔር ሆይ፥ እስከ መቼ ትረሳኛለህ? የምትረሳኝ ለዘለዓለም ነውን? እስከ መቼስ ከእኔ ትሰወራለህ?


ከባሕሩ መናወጥ የተነሣ የሚያስገመግመውን የማዕበል ድምፅ ጸጥ ታደርጋለህ፤ የሕዝቦችንም ሁከት ዝም ታሰኛለህ።


ጠላቶችህ “ድል አደረግን” ብለው በቤተ መቅደስህ ውስጥ ይደነፋሉ፤ በዚያም የድል ምልክት የሆነውን ዐርማቸውን ተክለዋል።


በእኔ ላይ ስለ መቈጣትህና ስለ ልብህ ትዕቢት ሁሉ ሰምቼአለሁ፤ ስለዚህ አሁን በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህም ልጓም አግብቼ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።”


ጠላቶቻችሁ ሁሉ በእናንተ ላይ አፋቸውን ይከፍታሉ፤ ያሽሟጥጣሉ ጥርሳቸውን ያፋጫሉ፤ እንዲህ ሲሉም ይጮኻሉ፦ “ደመሰስናቸው! እሰይ ይህ የምንመኘው ቀን ነበር! በመጨረሻም አየነው።”


“ተነሥተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ እኔ የሕዝብዋን ክፋት ተመልክቼአለሁ። ድምፅህንም ከፍ አድርገህ እርስዋን በመገሠጽ ተናገር።”


እነርሱ በበጉ ላይ ጦርነት ይከፍታሉ፤ ነገር ግን በጉ የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ ድል ይነሣቸዋል፤ ከእርሱ ጋር ያሉት የተጠሩ የተመረጡና የታመኑ ናቸው።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች