11 ለምን አትቀጣቸውም? ለምንስ ዝም ብለህ ትተዋቸዋለህ?
11 እጅህን ለምን ትሰበስባለህ? ቀኝ እጅህን ለምን በብብትህ ሥር ታቈያለህ?
11 እጅህንም ለምን ትመልሳለህ? ቀኝ እጅህንም ለምን በብብትህ መካከል ታቆያለህ?
ጌታ ሆይ! ንቃ! ስለምንስ ታንቀላፋለህ? ተነሥ! ለዘለዓለም አትተወን!
አምላክ ሆይ! ከዚህ ሁሉ በኋላ አንዳች ነገር አታደርግምን? ዝም ብለህስ በኀይለኛ ቅጣት ትቀጣናለህን?
በኀይለኛ ቊጣው የእስራኤልን ኀይል ሁሉ አዳከመ፤ ጠላትም እያየ ለእነርሱ የሚሰጠውን ድጋፍ አቋርጦ፥ በያዕቆብም ዘር ላይ እንደሚንበለበል እሳት ቊጣውን አቀጣጠለ፤ ቊጣው ጐረቤቶቹንም ሁሉ አወደመ።
ከጦርነት የተረፉት ወደ ሰፈራቸው በተመለሱ ጊዜ የእስራኤል መሪዎች እንዲህ አሉ፤ “ዛሬ ፍልስጥኤማውያን እኛን ድል ያደርጉ ዘንድ እግዚአብሔር ስለምን ፈቀደላቸው? ከእኛ ጋር በመሄድ ከጠላቶቻችን እጅ ያድነን ዘንድ እንግዲህ እንሂድና የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ከሴሎ እናምጣ።”