Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 37:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 በትዕግሥት ጸንተህ እግዚአብሔር የሚያደርገውን ለማየት ተጠባበቅ፤ ሌሎች ሰዎች ክፉ ሐሳባቸው ቢሳካላቸው አትበሳጭ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 በእግዚአብሔር ፊት ጸጥ በል፤ በትዕግሥትም ተጠባበቀው፤ መንገዱ በተቃናለት፣ ክፋትንም በሚሸርብ ሰው ልብህ አይሸበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በጌታ ጽና በተዕግሥትም ጠብቀው። መንገዱም በቀናችለትና በሚያደባ ሰው አትቅና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ነፍሴ ስድ​ብን ጠግ​ባ​ለ​ችና፥ ለሥ​ጋ​ዬም ድኅ​ነ​ትን አጣሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 37:7
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በንጉሡም ትእዛዝ ዐዋጁ ሱሳ ተብላ በምትጠራው መናገሻ ከተማ በይፋ ተገልጦ እንዲታይ ተደረገ፤ ፈጣኖች የሆኑ ሯጮችም ወደየአገሩ መልእክቱን አደረሱ፤ መናገሻ ከተማይቱ ሱሳ ታውካ ሳለች፥ ንጉሡና ሃማን በአንድነት ተቀምጠው የወይን ጠጅ ይጠጡ ነበር።


“ምንም እንኳ እግዚአብሔርን አላየውም ብትል ጉዳይህ በእርሱ ፊት ስለ ሆነ በትዕግሥት ልትጠብቀው ይገባል።


በእግዚአብሔር ታመን፤ በርታ፤ ተስፋ አትቊረጥ፤ በእግዚአብሔር ታመን።


እንዲረዳኝ በትዕግሥት ጌታን ተጠባበቅሁት። ወደ እኔም መለስ ብሎ ጸሎቴን ሰማ።


ስለ መሥዋዕትህና ዘወትር ስለምታቀርበው የሚቃጠል መባ አልወቅስህም።


የሚያድነኝ እርሱ ብቻ ስለ ሆነ፥ እግዚአብሔርን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።


እግዚአብሔርን ብቻ ጸጥ ብዬ እጠብቃለሁ፤ ተስፋዬም የሚመጣው ከእርሱ ነው።


ክፉ ያደረገብህን ሰው አንተም መልሰህ ክፉ አታድርግበት፤ በእግዚአብሔር ታመን፤ እርሱም ይታደግሃል።


በአንድ አገር ግፍ ሲሠራና መብት በመንፈግ ፍትሕ ሲጓደል ባየህ ጊዜ አትደነቅ፤ እያንዳንዱ ገዥ የበላይ ተመልካች አለው፤ ከሁሉም በላይ የሆነ ሌላ ተመልካች ደግሞ አለ።


የእስራኤል ቅዱስ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በመመለስና በማረፍ ደኅንነትን ታገኛላችሁ፤ ጸጥ በማለትና በመታመን ኀይል ታገኛላችሁ፤ እናንተ ግን እምቢ አላችሁ።


ምንም እንኳ እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ላይ ፊቱን ቢመልስባቸውም እኔ በእርሱ ላይ እተማመናለሁ።


እግዚአብሔር ሆይ! ከአንተ ጋር በምከራከርበት ጊዜ ሁሉ አንተ ትክክለኛ ነህ፤ አሁን ግን ስለ ትክክለኛ ፍርድ ጥያቄ አለኝ፤ የኃጢአተኛ ሕይወት የተቃና የሚሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? አታላዮችስ ሁሉ ነገር የሚሳካላቸው ስለምንድን ነው?


“የሶርያ ንጉሥ የፈለገውን ሁሉ ይፈጽማል፤ ራሱንም ከአማልክት ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ከአማልክት ሁሉ በላይ ባለው አምላክ ላይ ከዚህ በፊት ተሰምቶ የማይታወቅ የስድብ ቃል ይናገራል፤ የታቀደው ሁሉ መደረግ ስላለበት የእግዚአብሔር የቊጣው ቀን እስኪደርስ ድረስ ይሳካለታል።


የባሕሩም ማዕበል እየበረታ በመሄዱ መርከበኞቹ “ይህ ማዕበል ጸጥ እንዲል በአንተ ላይ ምን ብናደርግ ይሻላል?” ሲሉ ጠየቁት።


ምክንያቱም ራእዩ የተወሰነለትን ጊዜ ይጠብቃል፤ እርሱም የሚናገረው የሚፈጸምበትን ቀን ነው፤ ሐሰትም የለበትም፤ ጊዜ የሚወስድ ቢመስልም ጠብቅ፤ በእርግጥ ይደርሳል፤ አይዘገይምም።


ተስፋ ካልቈረጥን ወቅቱ ሲደርስ መከር ስለምንሰበስብ መልካም ሥራን ከመሥራት አንስነፍ።


እግዚአብሔር አሞራውያንን ለእስራኤላውያን አሳልፎ በሰጠበት ቀን ኢያሱ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገረ፤ እርሱም በእስራኤል ፊት እንዲህ አለ፦ “ፀሐይ በገባዖን፥ ጨረቃም በኤሎን ሸለቆ ላይ ይቁሙ” አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች