Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 143:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ጠላቴ በማሳደድ ተከታተለኝ፤ በጨለማ ውስጥም አስሮ አጐሳቈለኝ፤ ከብዙ ዘመናት በፊት እንደ ሞቱ ሰዎች ሆኜአለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ጠላት እስከ ሞት አሳድዶኛል፤ ሕይወቴንም አድቅቆ ከዐፈር ቀላቅሏል፤ ቀደም ብለው እንደ ሞቱትም፣ በጨለማ ውስጥ አኑሮኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ጠላት ነፍሴን አሳድዶአታል፥ ሕይወቴንም በምድር ላይ አጐስቁሎአታል፥ ቀድሞ እንደ ሞተ ሰው በጨለማ አኑሮኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 አቤቱ፥ ለእ​ርሱ ትገ​ለ​ጥ​ለት ዘንድ ሰው ምን​ድን ነው? ታስ​በው ዘን​ድስ የሰው ልጅ ምን​ድን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 143:3
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢዮአብም “ታዲያ ካየኸው ለምን ወዲያውኑ አልገደልከውም? ይህን አድርገህ ቢሆን ኖሮ እኔ ራሴ ዐሥር ጥሬ ብርና አንድ ዙር ዝናር በሸለምኩህ ነበር” ሲል መለሰለት።


እንደገናም አበኔር “እኔን ማሳደድህን ተው! ለምን እንድገድልህ ትገፋፋኛለህ? አንተንስ ብገድል የወንድምህን የኢዮአብን ፊት እንዴት ማየት እችላለሁ?” አለው።


በጣም ተስፋ የቈረጥሁ ስለ ሆነ እንድትረዳኝ ወደ አንተ ስጮኽ ስማኝ፤ እጅግ በርትተውብኛልና ከጠላቶቼ አድነኝ።


እኔን ለመግደል የሚፈልጉ ሁሉ ኀፍረትና ውርደት ይድረስባቸው! በእኔ ላይ የሚያሤሩም ሁሉ ተዋርደው ወደ ኋላቸው ይመለሱ!


ሞገደኞች አደጋ ሊጥሉብኝ ተነሡ፤ ጨካኞች ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ፤ ስለ እግዚአብሔርም አያስቡም።


ጠላቴ አሳዶ ይያዘኝ! እስከ ሞት ድረስ ይርገጠኝ በአቧራም ላይ ጥሎ ክብር ያሳጣኝ!


እግዚአብሔር ሆይ! በቊጣህ ተነሥ፤ የጠላቶቼንም ቊጣ አስወግድ፤ ፍርድ እንዲስተካከል ባዘዝከው መሠረት እኔን ለመርዳት ተነሥ፤


ከብዙ ጊዜ በፊት እንደ ሞተ ሰው በጨለማ ውስጥ እንድቀመጥ አስገደደኝ።


እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! የእስራኤል ሕዝብ እኮ ልክ እንደእነዚህ አጥንቶች ናቸው፤ እነርሱ ‘እነሆ፥ አጥንቶቻችን ደርቀዋል፤ ተስፋ ቈርጠናል፤ የእኛ ጉዳይ አልቆለታል’ ይላሉ።


ጠላቴ ሆይ! እኔ ብወድቅም እንኳ እንደገና እነሣለሁና በእኔ ደስ አይበልህ፤ አሁን በጨለማ ውስጥ ብሆንም እግዚአብሔር ያበራልኛል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች