Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 119:104 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

104 ከሕግህ ማስተዋልን አግኝቼአለሁ፤ ስለዚህ የሐሰት መንገድን ሁሉ እጠላለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

104 ከመመሪያህ ማስተዋልን አገኘሁ፤ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ሁሉ ጠላሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

104 ከትእዛዝህ የተነሣ አስተዋልሁ፥ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ጠላሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 119:104
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰዎችን ጠቢባን የሚያደርጋቸው ሽምግልና አይደለም፤ ትክክለኛውንም ነገር ለማስተዋል የሚረዳቸው የዕድሜ ብዛት አይደለም።


ክፉ ነገር ሲደረግ አይቼ ዝም አልልም፤ ከእግዚአብሔር የራቁ ሰዎች የሚያደርጉትን ሁሉ እጠላለሁ፤ ከቶም አልተባበራቸውም።


ትእዛዞችህን ሁሉ ስለምፈጽም፥ ከሽማግሌዎች ሁሉ የበለጠ አስተዋይነት አለኝ።


የአንተ ትእዛዞች ትክክል መሆናቸውን ስለማምን የሐሰትን መንገድ ሁሉ እጠላለሁ።


ሐሰትን እጠላለሁ፤ እጸየፋለሁም፤ ሕግህን ግን እወዳለሁ።


ሕግህን ግለጥልኝ፤ እኔም አከብረዋለሁ፤ በሙሉ ልቤም እጠብቀዋለሁ።


ትእዛዝህ መቼም ከአእምሮዬ ስለማይጠፋ፥ ከጠላቶቼ ሁሉ ይልቅ እኔን አስተዋይ ያደርገኛል።


በመኝታውም ላይ ሳለ ተንኰልን ያቅዳል፤ ራሱን ወደ ክፉ መንገድ ይመራል። ክፉውን ነገር አያስወግድም።


እግዚአብሔር ክፉ ነገርን የሚጠሉትን ሁሉ ይወዳል፤ ታማኞች አገልጋዮቹን ያድናቸዋል፤ ከክፉ መንፈስ ኀይልም እንዲያመልጡ ያደርጋቸዋል።


አንተ “ትክክለኛ መንገድ ነው” ብለህ የምታስበው ወደ ሞት ይመራህ ይሆናል።


ክፉ ነገርን መጥላት እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ እኔ ትዕቢትንና ዕብሪትን እጠላለሁ፤ ክፉ መንገድንና ጠማማ ንግግርን አልወድም


ክፉውን ነገር ጥሉ፤ መልካም የሆነውን ነገር ውደዱ፤ በየፍርድ አደባባዩም ፍትሕ እንዳይጓደል አድርጉ፤ ምናልባት የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ለተረፉት የእስራኤል ሕዝብ ምሕረት ያደርግላቸው ይሆናል።


“በጠባብዋ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚያስገባው በር ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነው። ወደዚያ የሚገቡትም ሰዎች ብዙዎች ናቸው።


ግብዝነት የሌለበት እውነተኛ ፍቅር ይኑራችሁ፤ ክፉውን ነገር ጥሉ፤ መልካሙን ነገር ተከተሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች