Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 10:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እግዚአብሔር ደጋግ ሰዎችን እንዲራቡ አያደርግም፤ ክፉዎች ግን የተመኙትን እንዳያገኙ ያደርጋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እግዚአብሔር ጻድቁ እንዲራብ አያደርግም፤ የክፉዎችን ምኞት ግን ያጨናግፋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ጌታ የጻድቁን ነፍስ አያስርብም፥ የክፉዎችን ምኞት ግን ይገለብጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እግዚአብሔር ጻድቅት ነፍስን አያስርብም፤ የኃጥኣንን ሕይወት ግን ከምድር ያስወግዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 10:3
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለአሞራ እንደሚጣል ምግብ ይጣላል፤ የሚጠፋበት ጨለማው ቀን እንደ ቀረበበት ያውቃል።


በእግዚአብሔርም የቊጣ ቀን የቤቱ ንብረት ሁሉ በጐርፍ ተጠራርጎ ይወሰዳል።


በራብ ዘመን በሕይወት ያኖርሃል። በጦርነትም ጊዜ ከሞት ያድንሃል።


አምላክ ሆይ! አንተ ግን ችግርንና ጭንቀትን አይተህ ልታስወግዳቸው መፍትሔ ታዘጋጃለህ፤ ችግረኛ ራሱን ለአንተ ይሰጣል፤ አንተም የሙት ልጆችን ትረዳለህ።


ክፉዎች ይህን አይተው ይቈጣሉ፤ ተስፋ በመቊረጥም ጥርሳቸውን ያፋጫሉ፤ የክፉዎችም ምኞት ከንቱ ይሆናል።


ይህም የሚሆነው ከሞት ሊያድናቸውና ከራብም ሊጠብቃቸው ነው።


ክፉ ቀን ሲመጣ ችግር አይደርስባቸውም፤ በራብ ዘመንም በቂ ምግብ በማግኘት ይጠግባሉ።


ከወጣትነት እስከ ሽምግልና ኖሬአለሁ፤ ታዲያ፥ እግዚአብሔር ደጉን ሰው ሲተወው፥ ልጆቹም ምግብ አጥተው ሲለምኑ፥ ከቶ አይቼ አላውቅም።


በእግዚአብሔር ታምነህ መልካምን አድርግ፤ በምድሪቱም በሰላም ትኖራለህ።


እውነተኞች ሊበሉ የሚፈልጉትን ያኽል ያገኛሉ። ኃጢአተኞች ግን ዘወትር ይራባሉ።


ችግር ሲመጣ ክፉዎች ይወድቃሉ፤ ጻድቃን ግን በታማኝነታቸው ይጠበቃሉ።


ስስታም ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ሰው ግን ይበለጽጋል።


አንድ ሰው ሕግን ባያከብር ጸሎቱ በእግዚአብሔር ዘንድ አጸያፊ ይሆናል።


በከፍተኛ ቦታ ላይ ይኖራሉ። ከለላቸውም እንደ ቋጥኝ ምሽግ ይሆናል ምግባቸውንም በጊዜው ያገኛሉ፤ የሚጠጡትንም ውሃ አያጡም።


እግዚአብሔር ቊጣውን በሚገልጥበት በዚያን ቀን ሰዎችን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ እንደ እሳት ባለው ቅናቱ ምድር ሁሉ ትጠፋለች፤ ይህም የሚሆነው በዓለም የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በድንገት የሚያልቁ ስለ ሆነ ነው።


ይልቅስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ፈልጉ፤ እነዚህም ነገሮች ሁሉ ይጨመሩላችኋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች