Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 6:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 “ናዝራዊው የተቀደሰውን ጠጒሩን ከተላጨ በኋላ ካህኑ የተቀቀለውን አውራ በግ ወርች፥ በመሶብ ውስጥ ካለው አንድ ኅብስትና አንድ ስስ ቂጣ ወስዶ ናዝራዊ በሆነው ሰው እጆች ላይ ያኖረዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 “ ‘ናዝራዊው ተስሎ የተለየበትን ጠጕር ከተላጨ በኋላ፣ ካህኑ የተቀቀለውን የአውራውን በግ ወርች እንዲሁም ከመሶቡ ላይ እርሾ የሌለበትን አንድ ወፍራምና አንድ ስስ ቂጣ ወስዶ ናዝራዊው ያስይዘው

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ካህኑም የተቀቀለውን የአውራውን በግ ወርች፥ ከሌማቱም እርሾ ያልገባበትን አንድ የቂጣ እንጐቻ እርሾም ያልገባበትን አንድ ስስ ቂጣ ይወስዳል፥ የተቀደሰውንም የራስ ጠጉር ከተላጨ በኋላ በናዝራዊው እጆች ላይ ያኖራቸዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ካህ​ኑም የተ​ቀ​ቀ​ለ​ውን የአ​ው​ራ​ውን በግ ወርች፥ ከሌ​ማ​ቱም አንድ ቂጣ እን​ጎቻ፥ አን​ድም ስስ ቂጣ ይወ​ስ​ዳል፤ የተ​ሳ​ለ​ው​ንም የራስ ጠጕር ከተ​ላጨ በኋላ በባ​ለ​ስ​እ​ለቱ እጆች ላይ ያኖ​ራ​ቸ​ዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ካህኑም የተቀቀለውን የአውራውን በግ ወርች፥ ከሌማቱም አንድ ቂጣ እንጐቻ አንድም ስስ ቂጣ ይወስዳል፥ የተለየውንም የራስ ጠጕር ከተላጨ በኋላ በናዝራዊው እጆች ላይ ያኖራቸዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 6:19
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦


እርሱንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቅርብ፤ የእንስሳውንም ስብ ከፍርምባው ጋር በመወዝወዝ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርጎ ያቅርብ።


ይህን ሁሉ ምግብ ወስዶ ለአሮንና ለልጆቹ በእጃቸው አስያዛቸው፤ አነርሱም በመወዝወዝ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርገው አቀረቡት።


“ሙሴም አሮንንና ልጆቹን እንዲህ አላቸው፤ ሥጋውን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ቀቅሉት፤ አሮንና ልጆቹ ይብሉት ብዬ እንዳዘዝኩት ያን በመሶብ ውስጥ ካለው የተቀደሰ ኅብስት ጋር ብሉት።


“ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገር፦ ወንድ ወይም ሴት ማንኛውም ሰው ራሱን ለእግዚአብሔር በመለየት ናዝራዊ ለመሆን ስእለት ቢያደርግ፥


ከዚህም በቀር ጮማው ከመቃጠሉ በፊት የካህኑ አገልጋይ መሥዋዕቱን ወደሚሠዋው ሰው መጥቶ “ካህኑ ያንተን የተቀቀለ ሥጋ ሳይሆን ጥሬ ሥጋ ስለሚፈልግ ለእርሱ እንድጠብስለት ሥጋ ስጠኝ” ይለው ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች