Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 35:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እነዚህም ከተሞች የሌዋውያን ይዞታ ሆነው እነርሱ ይኖሩባቸዋል፤ የግጦሽ መሬቱም ለከብቶቻቸውና ለሌሎች እንስሶቻቸው ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከተሞቹ ለእነርሱ መኖሪያ፣ የግጦሽ መሬቱ ለከብቶቻቸው፣ ለበግና ለፍየል መንጎቻቸውና ለሌሎቹም እንስሶቻቸው ይሆናሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እንዲቀመጡባቸውም ከተሞቹ ለእነርሱ ይሆናሉ፤ መሰማሪያቸውም ለከብቶቻቸው ለእንስሶቻቸውም እነርሱም ላሏቸው ነገሮች ሁሉ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ከተ​ሞ​ቹም ለእ​ነ​ርሱ መኖ​ሪያ ይሆ​ናሉ፤ መሰ​ማ​ር​ያ​ቸ​ውም ለከ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ለእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ቸው ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እነርሱም በከተሞቹ ውስጥ ይቀመጣሉ፤ መሰምርያቸውም ለከብቶቻቸው ለእንስሶቻቸውም ለእነርሱም ላለው ሁሉ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 35:3
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓምና በእርሱ እግር የተተኩት ዘሮቹ ሌዋውያንን የእግዚአብሔር ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉ ስላልፈቀዱላቸው ሌዋውያን ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም የመጡት የግጦሽ ቦታዎቻቸውንና የቀረውንም ንብረታቸውን ሁሉ ትተው ነው።


ከዚህም ክልል ውስጥ የእያንዳንዱ ማእዘን ርዝመት አምስት መቶ ክንድ ሆኖ አራት ማእዘን ያለው አንድ ቦታ ለቤተ መቅደሱ ይመደባል፤ በዚህም ክልል ዙሪያ ስፋቱ ኀምሳ ክንድ የሆነ ክፍት ቦታ ይኖራል።


“እስራኤላውያን ድርሻቸው ከሆነ ርስት ለሌዋውያን የሚኖሩባቸውን ከተሞችንና በከተሞቹም ዙሪያ የግጦሽ መሬት እንዲሰጡአቸው ንገር።


የግጦሽ መሬቱ ከከተማው ቅጽር ግንብ በሁሉ አቅጣጫ እስከ አራት መቶ ኀምሳ ሜትር ይስፋ።


“አንድ ሌዋዊ ከሚኖርበት ከማንኛውም የእስራኤል ከተማ እግዚአብሔር ወደሚመርጠው ቦታ ለመምጣት ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖረው፥


በይሁዳ ተራራማ አገር ያለችውን ቂርይትአርባቅ የምትባለውን ከተማ፥ በዙሪያዋ ካለው የግጦሽ መሬት ጋር ሰጡአቸው፤ እርስዋም ኬብሮን ናት፤ ይህም አርባቅ የዐናቅ አባት ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች