Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 30:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ባልዋ የሞተባት ሴት ወይም ከባልዋ የተፋታች ሴት ማንኛቸውንም ስእለት ሆነ ወይም ከአንድ ነገር ለመከልከል የገባችውን ቃል መፈጸም አለባት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “ባሏ የሞተባት ወይም ከባሏ የተፋታች ሴት የትኛውም ስእለቷ ወይም የገባችበት ግዴታ ሁሉ የጸና ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 “ባልዋ የሞተባት ወይም ከባልዋ የተፋታች ሴት ግን ስእለትዋ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ሁሉ ይጸኑባታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 “ባልዋ የሞ​ተ​ባት ወይም የተ​ፋ​ታች ግን ስእ​ለ​ቷና ራስ​ዋን ያሰ​ረ​ች​በት መሐላ ይጸ​ኑ​ባ​ታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ባልዋ የሞተባት ወይም የተፋታች ግን ስእለትዋ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ይጸኑባታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 30:9
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ካህናት ለአምላካቸው ተለይተው የተቀደሱ ስለ ሆኑ፥ አመንዝራ የነበረች ሴት፥ ወይም ክብረ ንጽሕናዋ የተደፈረ ልጃገረድ ወይም አግብታ የፈታች ሴት አያግቡ፤


ባል ያገባች ሴት ስእለት ብትሳል ወይም ከአንድ ነገር ለመከልከል በመሐላ ቃል ብትገባ፥


ባልዋ ስለ ጉዳዩ ሰምቶ ከከለከላት ግን የመፈጸም ግዴታ የለባትም፤ ስእለትዋን ለመፈጸም ያልቻለችው ባልዋ ስለ ከለከላት በመሆኑ እግዚአብሔር ይቅርታ ያደርግላታል።


ከዚህም በኋላ ዕድሜዋ ሰማኒያ አራት ዓመት እስኪሆን ድረስ ከቤተ መቅደስ ሳትለይ በጾምና በጸሎት ቀንና ሌሊት እግዚአብሔርን ታገለግል ነበር።


ለምሳሌ፥ ያገባች ሴት ባልዋ በሕይወት እስካለ ድረስ ከእርሱ ጋር በሕግ የታሰረች ናት፤ ባልዋ ከሞተ ግን ከታሰረችበት ሕግ ነጻ ናት።


እንደገናም ሌላ ባል ታገባ ይሆናል፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች