Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 26:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 የምናሴ ነገድ ተወላጆች ማኪር ገለዓድን ወለደ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 የምናሴ ዘሮች፤ በማኪር በኩል፣ የማኪራውያን ጐሣ፤ ማኪርም የገለዓድ አባት ነው፤ በገለዓድ በኩል፣ የገለዓዳውያን ጐሣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 የምናሴ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከማኪር የማኪራውያን ወገን፤ ማኪርም ገለዓድን ወለደ፤ ከገለዓድ የገለዓዳውያን ወገን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ከኮ​ቤር ልጆች፤ ከከ​ቤር የከ​ቤ​ራ​ው​ያን ወገን፥ ከሜ​ል​ክ​ያል የሜ​ል​ክ​ያ​ላ​ው​ያን ወገን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 የምናሴ ልጆች፤ ከማኪር የማኪራውያን ወገን፤ ማኪርም ገለዓድን ወለደ፤ ከገለዓድ የገለዓዳውያን ወገን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 26:29
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያዕቆብ ግን እጆቹን በማመሳቀል አስተላልፎ ቀኝ እጁን በታናሹ በኤፍሬም ራስ ላይ፥ ግራ እጁን በበኲሩ በምናሴ ራስ ላይ አኖረ።


የኤፍሬምንም ልጆችና የልጅ ልጆች እስከሚያይ ድረስ ቈየ፤ ከምናሴ የተወለደውንም የማኪርንም ልጆች እንደ ልጆቹ አድርጎ ተቀበላቸው።


ሔጽሮን ሥልሳ ዓመት ሲሞላው የገለዓድ እኅት የነበረችውን የማኪርን ልጅ አግብቶ ሰጉብ የተባለውን ወንድ ልጅ ወለደ፤


የዮሴፍ ልጅ ምናሴ የወለደው የማኪር ልጅ የገለዓድ ጐሣ የሆኑት የቤተሰብ አለቆች ወደ ሙሴና ወደ ሌሎቹም የእስራኤል ሕዝብ አለቆች ቀርበው እንዲህ አሉ፤


“ገለዓድንም ከምናሴ ነገድ ወገን ለሆነው ለማኪር ቤተሰብ ሰጠሁ፤


ይህ የዮሴፍ በኲር ልጅ የነበረው የምናሴ ነገድ ድርሻ የሚከተለው ነው። የምናሴ በኲር ልጅ የገለዓድ አባት ማኪር የጦር ጀግና ስለ ነበረ ገለዓድና ባሳን በርስትነት ተሰጠው።


ቀድሞ ዐማሌቃውያን ይኖሩበት ከነበረው ከኤፍሬም ወታደሮች መጡ፤ ሌሎችም ከብንያም መጡ። ከማኪር መሪዎች፥ ከዛብሎንም በትረ መንግሥትን የሚይዙ መጡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች