Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 18:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ይህም ልዩ መባ አንድ ገበሬ ከአዲስ እህል ወይም የወይን ጠጅ ዐሥራት አውጥቶ እንደሚሰጠው ዐይነት ሆኖ ይቈጠርላችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ቍርባናችሁም ከዐውድማ እንደ ገባ እህል ወይም ከመጭመቂያ እንደ ወጣ ወይን ሆኖ ይቈጠርላችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እንደ ስጦታ የምታቀርቡት ቁርባናችሁም እንደ አውድማው እህልና እንደ ወይን መጭመቂያው ሙላት ይቈጠርላችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 መባ​ች​ሁም እንደ እህል ዐው​ድ​ማው ስን​ዴና እንደ ወይን መጭ​መ​ቂ​ያው ፍሬ ይቈ​ጠ​ር​ላ​ች​ኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 የማንሣት ቍርባናችሁም እንደ አውድማው እህልና እንደ ወይን መጭመቂያው ፍሬ ይቈጠርላችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 18:27
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ “አጣድ” ተብላ ወደምትጠራው አውድማ ደረሱ፤ እዚያም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በመጮኽ አለቀሱ፤ ዮሴፍም እዚያ ሰባት ቀን ሙሉ የሐዘን ውሎ አደረገ።


ንጉሡም “እግዚአብሔር ሊረዳሽ ካልፈቀደ እኔ ምን ዐይነት ርዳታ ልሰጥሽ እችላለሁ? ከአውድማው ወይስ ከወይን መጭመቂያው? ምን ያለኝ ይመስልሻል?


ይኸውም ከአዲስ እህል የተጋገረው የመጀመሪያው ኅብስት ለእግዚአብሔር ልዩ መባ ሆኖ ይቅረብ፤ ይህም ከምትወቁት እህል በማንሣት እንደምታመጡት ልዩ መባ በተመሳሳይ ይቅረብ፤


“ለሌዋውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘እግዚአብሔር ድርሻችሁ አድርጎ የሚሰጣችሁን ዐሥራት ከእስራኤላውያን በምትቀበሉበት ጊዜ፥ እናንተም በበኩላችሁ ከዚያው ከተቀበላችሁት የዐሥራት ዐሥራት በማውጣት ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርጋችሁ አቅርቡ።


በዚህ ዐይነት እናንተም ከእስራኤላውያን ከምትቀበሉት ዐሥራት ሁሉ፥ ለእግዚአብሔር የሚሆነውን ልዩ መባ ታቀርባላችሁ፤ ለእግዚአብሔር የምታመጡትን ይህን ልዩ መባ ለካህኑ አሮን ታስረክቡታላችሁ።


ምርጥ የሆነውን ነገር በምትሰጡበት ጊዜ ገበሬ መባውን ከሰጠ በኋላ የተረፈውን ለራሱ እንደሚያስቀር እናንተም የተረፈውን ለራሳችሁ ታስቀራላችሁ።


እግዚአብሔር አምላክህ ከሰጠህ በረከት፥ ማለት፥ ከበጎች፥ ከእህልና ከወይን በልግሥና ስጠው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች