Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 8:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ይህንንም በማድረጉ በነቢዩ ኢሳይያስ፥ “እርሱ ደዌአችንን ተቀበለ፤ ሕመማችንንም ተሸከመ” የተባለው ትንቢት ተፈጸመ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 በዚህም ኢሳይያስ እንዲህ ብሎ የተናገረው ትንቢት ተፈጸመ፤ “እርሱ ደዌያችንን ወሰደ፤ ሕመማችንንም ተሸከመ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ይህም በነቢዩ ኢሳይያስ “እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸከመ፤” የተባለው እንዲፈጸም ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 8:17
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብርሃምም የመሥዋዕቱን እንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፤ እርሱ ግን ቢለዋውንና እሳቱን ያዘ፤ ሁለቱም አብረው ሲሄዱ ሳለ፥


“በእውነት እርሱ ደዌአችንን ተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ እኛ ግን በእግዚአብሔር ተመትቶ እንደ ወደቀና እንደ ቈሰለ አድርገን ቈጠርነው።


ይህም ሁሉ የሆነው ጌታ እንዲህ ሲል በነቢይ አማካይነት የተናገረው እንዲፈጸም ነው፤


እዚያም ሄሮድስ እስኪሞት ድረስ ቈየ፤ ይህም የሆነው ጌታ በነቢይ “ልጄን ከግብጽ ጠራሁት” ያለው ቃል እንዲፈጸም ነው።


“ናዝራዊ ይባላል” ተብሎ በነቢያት የተነገረው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።


ፀሐይ ጠልቃ በመሸ ጊዜ ሰዎች በሽተኞችንና በአጋንንት የተያዙትን ሁሉ ወደ ኢየሱስ አመጡ።


ፀሐይ ስትጠልቅ ሰዎች በልዩ ልዩ ደዌ የተያዙባቸውን ሕመምተኞች ሁሉ ወደ ኢየሱስ አመጡ፤ እርሱም በእያንዳንዳቸው ላይ እጁን በመጫን ፈወሳቸው።


ኀይል የማገኘው ደካማ በምሆንበት ጊዜ ስለ ሆነ ስለ ክርስቶስ ስደክም፥ ስሰደብ፥ ስቸገር፥ ስሰደድ፥ ስጨነቅ ደስ ይለኛል።


ከኃጢአት ተለይተን በጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በመስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቊስል እናንተ ተፈውሳችኋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች