Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 20:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ሕዝቡም “ዝም በሉ!” ብለው ገሠጹአቸው፤ እነርሱ ግን “የዳዊት ልጅ ጌታ ሆይ! እባክህ ማረን!” እያሉ አብዝተው ጮኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ሕዝቡም በግሣጼ ቃል ዝም እንዲሉ ነገሯቸው፤ እነርሱ ግን አምርረው በመጮኽ፣ “ጌታ ሆይ፤ የዳዊት ልጅ ማረን!” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ሕዝቡም ዝም እንዲሉ ገሠጹአቸው፤ እነርሱ ግን “የዳዊት ልጅ፥ ጌታ ሆይ! ማረን” እያሉ አብዝተው ጮኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ሕዝቡም ዝም እንዲሉ ገሠጹአቸው፤ እነርሱ ግን “ጌታ ሆይ! የዳዊት ልጅ፥ ማረን” እያሉ አብዝተው ጮኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ሕዝቡም ዝም እንዲሉ ገሠጹአቸው፤ እነርሱ ግን፦ ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ፥ ማረን እያሉ አብዝተው ጮኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 20:31
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሱ ግን አንድም ቃል ሳይመልስላት ዝም አለ፤ በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው፥ “ይህች ሴት እየተከተለችን ስለምትጮኽ እባክህ አሰናብታት!” ሲሉ ለመኑት።


በዚያን ጊዜ እጁን በላያቸው ላይ ጭኖ እንዲጸልይላቸው ሰዎች ሕፃናትን ወደ ኢየሱስ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ሰዎቹን ገሠጹአቸው።


እነሆ፥ በመንገድ ዳር የተቀመጡ ሁለት ዕውሮች በዚያ በኩል የሚያልፈው ኢየሱስ መሆኑን በሰሙ ጊዜ፥ “ጌታ የዳዊት ልጅ ሆይ! እባክህ ማረን!” እያሉ ጮኹ።


ኢየሱስም ቆሞ ጠራቸውና “ምን እንዳደርግላችሁ ትፈልጋላችሁ?” አላቸው።


ኢየሱስ ከዚያ ቦታ ተነሥቶ ሲሄድ ሁለት ዕውሮች ተከተሉት፤ እነርሱም “የዳዊት ልጅ ሆይ! እባክህ ማረን!” እያሉ ይጮኹ ነበር።


ቀድመው እፊት እፊት ይሄዱ የነበሩት ሰዎች፦ “ዝም በል!” ብለው ገሠጹት። እርሱ ግን ድምፁን በይበልጥ ከፍ አድርጎ፦ “የዳዊት ልጅ ሆይ! እባክህ ማረኝ!” ይል ነበር።


እግዚአብሔርን ተግታችሁ በማመስገን ባለማቋረጥ ጸልዩ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች