Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 19:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ኢየሱስ ወደ እነርሱ ተመልክቶ “ይህ ነገር ለሰው የማይቻል ነው፤ ለእግዚአብሔር ግን ሁሉም ይቻለዋል” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ኢየሱስም አያቸውና፣ “ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉም ነገር ይቻላል” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ኢየሱስ ግን አያቸውና እንዲህ አላቸው “ይህ በሰው ዘንድ የማይቻል ነው፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ኢየሱስም እነርሱን ተመልክቶ “ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል፤” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ኢየሱስም እነርሱን ተመልክቶ፦ ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 19:26
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከቶ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? እንደ ነገርኩህ የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው።


እግዚአብሔር በኤልያስ አማካይነት በሰጠው ተስፋ መሠረት ዱቄቱ ከማኖሪያው ዕቃ፥ ዘይቱም ከማሰሮው አላለቀም።


“አምላክ ሆይ! አንተ ሁሉን ነገር ማድረግ እንደምትችል ዐውቃለሁ፤ የአንተንም ዕቅድ ማሰናከል የሚችል የለም።


ማዳን የእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፥ በረከትህ በሕዝብህ ላይ ይሁን።


እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ተናግሮአል፤ ኀይል የእግዚአብሔር መሆኑን ሁለት ጊዜ ሰምቼአለሁ።


“ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! በታላቁ ሥልጣንህና ኀይልህ ሰማይና ምድርን ፈጥረሃል፤ ከቶም የሚሳንህ ነገር የለም፤


“የሰው ዘር ሁሉ አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከቶ ለእኔ የሚሳነኝ ነገር አለን?


“በእነዚህ ቀኖች ከሕዝቡ ለተረፉት ይህ የማይቻል ነገር ቢመስልም እንኳ በውኑ ለእኔ የማይቻል ነገር አለን?


እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የእኔ የእግዚአብሔር ኀይል ውሱን ነውን? ቃሌ በእናንተ ዘንድ የሚፈጸም ወይም የማይፈጸም መሆኑን አሁን ታያለህ!”


ደቀ መዛሙርቱ ይህን በሰሙ ጊዜ በጣም ተገረሙና “ታዲያ፥ ማን ሊድን ይችላል?” አሉ።


በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ “እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከትለንሃል፤ ታዲያ፥ የምናገኘው ምን ይሆን?” አለ።


ኢየሱስም ወደ እነርሱ ተመልክቶ፦ “እርግጥ ይህ ነገር በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ይቻላል፤ ለእግዚአብሔር ሁሉ ነገር ይቻለዋል፤” አላቸው።


ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም።”


ኢየሱስ ግን፥ “በሰው ዘንድ የማይቻል ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል” አለ።


ከዚህ ሁሉ በኋላ እምነታቸውን ቢክዱ እነርሱ ለራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ እንደገና ስለሚሰቅሉትና በይፋ ስለሚያዋርዱት እነርሱን ወደ ንስሓ መመለስ አይቻልም።


ዮናታን ጋሻ ጃግሬ የሆነውን ወጣት “ና ወደ እነዚያ ወደ አልተገረዙት ወገኖች የጦር ሰፈር እንሻገር እግዚአብሔር ይረዳን ይሆናል፤ በብዙም ሆነ በጥቂት እግዚአብሔር ማዳን አይሳነውም” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች