Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 3:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ሰዎች እንዳያጣብቡት ጀልባ አዘጋጅተው እንዲያቀርቡለት ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የተሰበሰበውም ሕዝብ እንዳያጨናንቀው አነስተኛ የሆነ ጀልባ እንዲያዘጋጁለት ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ እንዳያስጨንቁት ጀልባ እንዲያዘጋጁለት ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሰዎቹም እንዳያጋፉት ታንኳን ያቆዩለት ዘንድ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ሰዎቹም እንዳያጋፉት ታንኳን ያቆዩለት ዘንድ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 3:9
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ሕዝቡን አሰናበተ፤ በጀልባም ተሳፍሮ ወደ መጌዶን ክፍለ ሀገር ሄደ።


ኢየሱስ እንደገና በባሕሩ አጠገብ ማስተማር ጀመረ። እጅግ ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ መጥተው በመሰብሰባቸው እርሱ በባሕሩ ላይ በነበረው ጀልባ ገብቶ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ሁሉ በባሕሩ ዳርቻ ነበሩ።


ከሕዝቡም ተለይተው ተሳፍሮበት በነበረው ጀልባ ኢየሱስን ይዘውት ሄዱ፤ ሌሎችም ጀልባዎች አብረው ነበሩ።


ኢየሱስ ከጀልባው እንደ ወረደ አንድ በርኩስ መንፈስ የተያዘ ሰው ወዲያውኑ ከመቃብር ቦታ ወጥቶ ተገናኘው።


ኢየሱስም ወዲያውኑ ኀይል ከእርሱ እንደ ወጣ ዐወቀ፤ ወደ ሕዝቡም ዘወር ብሎ፦ “ልብሴን የነካ ማን ነው?” ሲል ጠየቀ።


ስለዚህ ብቻቸውን ለመሆን በጀልባ ተሳፍረው ወደ አንድ ገለልተኛ ስፍራ፥ ሄዱ።


አንድ ቀን ኢየሱስ በጌንሳሬጥ ባሕር ዳር ቆሞ ሳለ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ቀርበው የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ይጋፉ ነበር።


ኢየሱስ ከጀልባዎቹ ወደ አንዲቱ፥ የስምዖን ወደሆነችው ገባ። ስምዖንንም “ይህችን ጀልባ ከምድር ወደ ባሕሩ እስቲ ጥቂት ፈቀቅ አድርግልኝ” አለው። ከዚህም በኋላ በጀልባዋ ላይ ተቀምጦ ሕዝቡን ያስተምር ጀመር።


ሰዎቹ ግን በግድ ወስደው ሊያነግሡት እንዳሰቡ ባወቀ ጊዜ ኢየሱስ ብቻውን እንደገና ራቅ ብሎ ወደ ኮረብታ ሄደ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች